Get Mystery Box with random crypto!

ካሊድም ቀጠለ ....እሺ ሌላኛዉ ደግሞ ስደዉል ብዙ ጊዜ ስልክ አታነሺም፡፡ አንስተሽም ቡሀላ እደዉ | ISLAMIC SCHOOL

ካሊድም ቀጠለ ....እሺ ሌላኛዉ ደግሞ ስደዉል ብዙ ጊዜ ስልክ አታነሺም፡፡ አንስተሽም ቡሀላ እደዉላለሁ ነበር የምትይኝ ..ስፈልጊ ስልኬን block ታረጊኝ ነበር..text ስልክልሽ አመልሽም ... መንገድ ላይም ፊት ትነሺኝ ነበር ...እያለ በደሉን በአንዴ ዘረገፈዉ ኮሌጅ መማር ከጀመርኩ  ጀምሮ የሶስቱንም አመቱን ብሶቱን አንድ ባንድ ነገረኝ ...
ከዛም አንቺስ ይሄን አድርገህኛል ይሄ ጥፋት አለብህ የምትይኝ አለ ?.....,እኔም የምለዉ የምመልሰዉ ሳጣ ምንም አላረከኝም ላለማለት አንድ ቀን callme back ልኬልህ እንድደዉልልኝ ፈልጌ አልመለስክልኝም አልኩት
......እሱም ሳቀ

መፍቱሀም ጥፋተኛ እሷ ናት ምን እንድትቀጣ ነዉ የምፈልገዉ ??? አለችዉ
ካሊድም >>>እኔ ልቤን ሰጥቻት ልቤን ጣለችብኝ ልቤን ከጣለችበት አንስታ ትስጠኝ<<<አለ

በጣምምም ደነገጥኩ ካሊድ እንደዚህ ይላል ብየ አስቤም ትዝም ብሎኝ አያዉቅም
.....እኔም እንዳልገባኝ ለማስመሰል ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ ??አልኩት
...መፍቱሀ ሰምተሻል በአንቺ ቤት ማደናቆርሽ ነዉ??.. ልቤን ሰጥቻት ጥለዋለች ብሏል ከጣልሽበት ሂደሽ ፈልገሽ አምጪ አለችኝ

....እኔም ወደ ካሊድ ዙሬ ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ?? ንገረኝ ዙሪያ ጥምጥም አትሂድ እያልኩ ፍጥጥ አርጌ ያዝኩት
.....ካሊድም ነዋል ዛሬ ተረጂኝ እባክሽ ከልቤ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ፍቃደኛ ከሆንሽ ላገባሽ እፈልጋለሁ  ልትመረቂ ሁለት ወር ነዉ የቀረሽ...,ታስታዉሽ እንደሇነ ገና ኮሌጅ ሳትመዘገቢ ላግባሸ ስልሽ አሁን መማር እፈልጋለሁ ነዉ ያልሽኝ...አሁን ትምህርት ጨሬሰሻል የቀረሽ የምረቃን proces ብቻ ነዉ
.....ስለዚህ ላገባሽ እፈልጋለሁ እና ፍቅሬን ተቀበይኝ ...በዚህ ሁለት ወር ዉስጥ እንግባባ ስለ እኔ ማጣራት የምፈልገዉ ነገር ካለ ከማንኛዉም ሰዉ ማጣራት ትችያለሽ ..,እኔ ግን ስለአንቺ ምንም የማጣራዉ የምጠይቀዉም የለም ዛሬም ነገም ብትይኝ አንቺን ለማግባት ዝግጁ ነኝ..,አለኝ

....እኔም ከአነጋገሩ እምቢ የምልበት ድፍረት አጣሁኝ.... አስቤበት ይሁን በድንጋጤ አላወኩትም ከአፌ ግን እሺ የምትል ሁለት ቃላት ተነፈስኩኝ

ካሊድ በጣም ደስ አለዉ የዛን ጊዜ የተደሰተዉ ደስታ በቃላት መግለፅ አልችልም ቁጭ ብድግ ነዉ እያለ የሚያወራዉ ጠፍቶታል፡፡ የሚያወራዉ ሲያጣ በቃ የዛሬ ሳምንት ጁምአ ምሳ ሰአት እንገናኛለን አለኝ
.....እኔም ኢንሻ አላህ አልኩት
ወደ ጂማ ከተማዉ ሳይመሽ ተመለስን...እቤቴ ድረስ በመኪና ሸኝቶኝ ተመለሰ፡፡



     እቤቴ ከገባሁ ቡሀላ እንደገና የረሳሁትን ማሰብ የማልፈልገዉ የአእምሮ ጥያቄ እየመጣ ያቃጭልብኝ ይዟል... መጨነቅ መጠበብ ሆነ ካሊድ ድንግል ነሽ ወይስ አይደለሽም ?? ብሎ ቢጠይቀኝ ምንድን ነዉ መልሴ??...እንዴትስ ነዉ የማስረዳዉ ???እያልኩ ስጨናነቅ እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ አደርኩኝ.....

የማይነጋ ለሊት የለም ጨለማ ለፀሀይ ቦታዋን አስረከበች ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ዘንድሮ ተመራቂ ስለሆንኩ coc እንዳልወድቅ ዝግጅት እያረኩ ነዉ.... ግን ካሊድ ይደዉልልኛል፡፡ በነዚህ ቀናት ዉስጥ በቀን ዉሰጥ በትንሹ ደወለ ከተባለ ቢያንስ 5 ጊዜ ሳይደዉል ቀርቶ አያቅም ፡፡
......እኔ ካሊድ ጋር ስናወራ ከበፊቱ ጀምሬ የምፈራዉ በማንነቴ ነዉ ..ሁሌም ሀሳቤ በዚህ ማንነቴ መጣላታችን አይቀርም እያልኩ አስባለሁ ፡፡ እንዴት እኔን ሊረዳኝ ይችላል??

ካሊድን እሺ ካልኩ ቡሀላ እንደ በፊቱ መጨናነቅ ይዣለሁ ...ካሊድን እንዴት ልራቅ??? ማንነቴን ላይቀበለኝ ይችላል እያልኩ ሳስብ ጨጓራ አለብኝ በጣም አመመኝ በሁለት ቀን ልዩነት ሀኪም ቤት እስከ መሄድ ደርሻለሁ.... ካሊድም ምን ሁነሽ ነዉ ያመመሽ ??ተሻለሽ ወይ ??እያለ በየሰአቱ ነበር የሚደዉለዉ....መልስ የሌለዉ ጥያቄ እንዴት ልመልስ በሆዴ ታምቆ ተቀምጧል...ካሊድ ቀላል ህመም ነዉ ይሻለኛል ብየ እመልስለታለሁ ......
ለዉጥ ሲኖረኝ ወደ ክላስ ሂጄ ለCoc ዝግጅት አደርጋለሁ፡፡

እንደዚህ እያለ ሳምንቱ አልፎ ጁምአ ደረሰ ... ካሊድ የጠራኝን ምሳ እረስቸዋለሁ ትምህርት አልገባሁም.. ጁምአ ለመስገድ ቀደም ብየ አጅፕ መስጊድ ገብቼ ቁርአን  ቀራሁ....ከዛም ጁምአ ተሰግዶ እንደጨረስን ....መፍቱሀ እኔም በተጨማሪ ሌሎች ሶስት ጓደኞቼ ጁምአ ጁምአ ምሳ የምንበላዉ አንድ ላይ ነዉ፡፡ በየተራ ሁላችንም እቤት እያዘጋጀን ዛሬ አንዷ ቤት ሳምንት ሌላ የጓደኛችን ቤት የእኔ ተራ ሲሆን እኛ ቤት እያልን ጁምአን ምሳ እንደዚህ ነዉ የምናሳልፈዉ...

ከዛም እኔ የካሊድን ቀጥሮ ረስቼ  መፍቱሀ ቤት ሆድኩ ፡፡ የሄድኩበትም ምክንያት የጁምአ ምሳ ተረኛ የሆነችዉ ጓደኛችን ቤት አብረን ለመሄድ ነዉ፡፡
መፍቱሀ ቤት እንደ ደረስኩ ...እሷ የምልብሰዉ በጣም የሚያምር ጅልባብ አምጥታ ይሄን ልበሽ አለችኝ
....እኔም ሰርግ ነዉ እንዴ የምንሄደዉ?? አልኳት...
ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዉ ይሄን ጅልባብ ስለብሺ ያምርብሻል ይሉኛል እኔም ሰርግ ሲኖረኝ የመፍቱሀን ጅልባብ ነዉ የምለብሰዉ
.....እሷም ጅልባቡን ልበሽ ከሰርግ በላይ ነዉ አለችኝ

ባጃጅ ገብተን እየሄድን...ካሊድ ደወለልኝ
..... የኔ ፍቅር እየመጣችሁ ነዉ ??? አለኝ
.........የት ነዉ የምንመጣዉ ?? አልኩት
....እሱም እኔ መኖሪያ ቤት አለኝ
ከዛም ተናድጄ ጆሮዉ ላይ ስልኩን ዘጋሁት


ከዛም መፍቱሀን እወንድ ቤት ነዉ እንዴ የምወስጂኝ ?? የሷሊህን ገጠመኝ ነግሬሽ እንዴት ትወስጂኛለሽ ??መፍቱሀ አሳልፈሽ ልሰጪኝ ነዉ እንዴ?? እያልኩ ባጃጅ ዉስጥ ሁኜ አለቀስኩኝ

መፍቱሀም ነዋል ተረጋጊ ምንም አትሆኝም ድብቅ ሚስጥር የለዉም ...እህቶቹ ምሳ አዘጋጅተዉ እየጠበቁን ከእነሱ ጋር ሊያስተዋውቅሽ ነዉ እንጂ ለሌላ አይደለም አለችኝ

ካሊድ የመጨረሻ ልጅ ነዉ ፡፡ ያገቡ ልጅ ያላቸዉ ታላቅ እህቶች አሉት ...ብዙ ጊዜ ስለእህቶቹ ስለነገረኝ እሺ ብየ ተረጋጋሁ እና እንባየን ጠረኩኝ ፡፡


ካሊድ መኖሪያ ቤት እንደደረስኩ ያየሁትን ማመን አቃተኝ ሰርፕራይዝ ነዉ የሆነብኝ ፡፡ የሒወቴ የመጀመሪያ የደስታ ጊዜ ይቺ ቀን ናት ብየ መናገር እችላለሁ የዚህን ቀን ደስታ ወላሂ መናገር አልችልም...አባቴ እኔን የተለያዩ ቦታ ወስዶ አዝናንቶኛል ...ግን የዚህን ቀን ደስታ እሩብ እንኳ አያክልም ...

ገና እቤቱ በር ላይ ስደርስ መፍቱሀ አይኔን አሰረችኝ
....እኔም ደነገጥኩኝ ምንድን ነዉ መፍቱሀ እየተፈጠረ ያለዉ ነገር አልገባኝም?? አልኳት
....መፍቱሀም በሂደት ይገባሻል አለችኝ...የካሊድ አንዱ እህቱ Video እየቀረፀችኝ ነዉ፡፡

መፍቱሀ እጄን ይዛኝ ፤ አይኔ እንደተጨፈነ ወደ ዉስጥ ገባሁኝ ...የቤቱ ሳሎኑ  በጣም ሰፊ ነዉ

ካሊድ እንዲህ አላት:- መፍቱሀ አሁን አይኗን ግለጫት አላት
-------መፍቱሀም አይኔን ገለጠችኝ .....ያየሁትን ማመን አቃተኝ እንደዚህ አይነት ሰርፕራይዝ በፊልም ለራሱ አይቼዉ አላቅም እንኳን በኔ ሒወት ከፊልም በላይ ነዉ የሆነብኝ
#ክፍል
ይ ...........ቀ........
.......,ጥ...........ላ..............ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•