Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ አንድ

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




..ነዋል ከቤተሰቦቼ ወጥቼ #ቤት_ተከራይቼ_ብቻየን_መኖር_ጀመርኩኝ አለኝ


በሌላ ቀን ሲደዉልልኝ ለቤቱ የገዛዉን ይነግረኛል .አንድ ቀን ቡፌ ገዛሁ ሌላቀን ቴሌቪዢን አረ ብዙ ነገር እያሟላ እንደሆነ ይነግረኛል፡፡ እኔንም በተለያዩ ቅኔዎች እንደሚወደኝ ይነግረኛል..ለምሳሌ አንቺን የመሰለ ልጅ ፈልጊልኝ ይሄ ቤት ብርድ ብርድ አለኝ ሀላሌ ናፈቀችኝ...ወይም እቃዉ ቤቱ ተሟሏ ምሳ
ቁርስ አዘጋጅታ እንብላ የምትል ጠፋች....ቤቱ ሙድ እየያዘብኝ ተቸገርኩ ብቻየን ሊወረኝ ነዉ...አንዳንዴም የገዛሇቸዉ የቤት እቃዎች ሳልጠቀምባቸዉ ሸረሪት ድር አደራበት እኮ ማን ይስራበት...እያለ በተለያየ ዘዴ እንደሚወደኝ እና በዘዴ እኔን ማግባት እንደሚፈልግ እየነገረኝ ይመስለኛል ባልሳሳት...ግን እንጃ ደግሞ የወንድ ፍቅር ከአፍ መች ያልፋል

ዘንድሮ መመረቂያ አይደል አፓረንት መዉጣት ግድ ነበር ከጂማ የሶስት ሰአታት መንገድ የሚሆን ሰካ የምትባል ገጠራማ ቦታ ጤና ጣቢያ ለሶስት ወር ጊዜ ወጣሁኝ እዛዉ ለ3ወር ቤት ጓደኞቼ እኔ መፍቱሀ እና ብሩክ ታይት ጋር አንድ ላይ ቤት ተከራይተን መኖር ጀመርን ፡፡ ላለመደዉ ሰዉ በጣም ይከብዳል በግድ አገሩን ተላመድኩት፡፡አይ ዱንያ
★★★ነብዩላህ ኑህ (ዐ.ሰ) ሊሞቱ በተቃረቡበት ጊዜ የሚከተለዉ ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር፡-እረጅም እድሜ የታደሉት ነብይ ሆይ!!!!ይህን አለም እንዴት ተመለከቷት??
ኑህ (ዐ.ሰ)ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲመልሱ ""ሁለት በሮች እንዳሉት ቤትና በአንዱ በር ገብቼ በሌላዉ በር የወጣሁ ያክል ሆና ነዉ ያገኘሆት .የሚል ምላሽ ሰጥተዋል
★★★ነብዩላህ ኑህ (ዐ.ሰ)ለራሳቸዉ በቀርቀሀ አነስተኛ ጎጆ ቀልሰዉ ነበር የሚኖሩት
ከዚህ የተሻለ ጠንካራ ቤት መስራት እየቻሉ..ለምን በዚህ ደካማ ጎጆ ዉስጥ ይኖራሉ ? ተብለዉ ሲጠየቁ
ነገ በሞት ይችን አለም ለሚለቅ ሰዉ ይህ ራሱ ሲበዛበት ነዉ ብለዋል፡፡
ዱንያ የዚህን ያህል ጭንቀት ደስታ ይፈራረቅብናል እንጂ የዚህን ያህል የሚጓጓላት ለሚኖር የሚናፈቅባት አይደለችም.. አላህ ልቦና ይስጠን!!!!!


አፓረንት ላይ ሁኜ ከካሊድ ጋር እናወራለን
...ሆስፒታሉ አንድ ቀን አዳር አንድ ቀን ደግም በቀን ነበር ተመድቤ የምሰራዉ፡፡
እዛ ስንሰራ አዳር እንቅልፍ እንዳይዘኝ ካሊድ ይደዉልልኛል አኩለ ለሊት እስኪያልፍ ስናወራ እናመሻለን ...ጉድ ነዉ ካርዱ ተገዝቶ መሆኑን እረስተን ከምንጭ ተጠልቆ የተሞላ ይመስል ትዝ አይለንም ፡፡


ካሊድ በሶስት ቀን ልዩነት ከጂማ ምግብና የሚጠጡ የተለያዩ ነገሮች ይዞልኝ ይመጣ እና በሩቁ ሰላም ናችሁ አብሽሩ ብሎን ይመለሳል፡፡ ካሊድ በስልክ ነዉ እንጂ ዘና ብሎ የማያወራኝ በአካል ስንገናኝ እንደተደገመት ሰዉ አፉ ይያያዛል ቶሎ ለመሄድ ነዉ የሚቸኩለዉ . ነዋል አብሽሪ አትፍሪኝ የምፈልጊዉ ከጂማ የሚመጣ ነገር ካለ ንገሪኝ ..እኔም እየመጣሁ አያችሇለሁ በሉ ቻዉ ብሎን ይሄዳል፡፡

ካሊድ እነዚህን ሶስት ወራት እየመጣ ገጠር ድረስ አይቶኝ አንዳንድ ነገር ይዞልኝ ይመጣል...በስልክም ማታ እንቅልፌ እንዳይመጣ እዛዉ ጤና ጣቢያ ሁኜ አሱ ጋር እያወራን እኩለ ለሊት ያልፋል፡፡፡

በዚህ ሶሰት ወራት አዲስ ነገር ተፈጥሯል ጓደኛችን ብሩክ ታይት በመፍቱሀ ምክር ደአዋ በፊትም ልቧ ወደ ኢስላም ያዘነበለ ነበር እስልምናን ተቀበለች በጣም ደስ አለን፡፡ እሷም ሙስሊም መሆኔን ለቤተሰቦቼ ሳልዉል ሳላድር ማሳወቅ አለብኝ አለችን..
ቆይ ተረጋጊ በሒደት ትነግሪያቸዋለሽ አሁን እስልምናን በደንብ እወቂ ብንላት
..ብሩክታይት ልንገራቸዉ እና ይለይልኝ ቤተሰቦቼ ከኢስላም ሀይማኖት አይበልጡብኝም ብላ እኛ ተረጋጊ ብንላት ልትሰማን አልቻለችም ... ለእናት እና ለአባቷ ስትደዉል...የገጠማት የማይታመን ነበር ሙስሊም ከሆንሽ እቤት እንዳትመጪ ብለዉ የወለደ አንጀታቸዉ ቆራጥ አመራር ገጠማት.እኛም ጭንቅ ጥብብ አለን ፡፡መፍቱሀም አትሰቢ እኔ ጋር ትኖሪያለሽ አብሽሪ አለቻት



አፓረንታችንን 3ወር ያህል ጨርሼ ተወልጄ ወደ አደኩበት አባጅፋር ሀገር ጂማ ከተማ ተመለስኩኝ ፡፡ ብሩክታይትም መፍቱሀ ቤተሰቦች ጋር አብራ መኖር ጀመረች
ከተመለስኩ ጀምሬ ካሊድ ጋር በስልክ እያወራን ነዉ....ሀሙስ ቀን እንደዚህ አለኝ

ነዋል ነገ ከጓደኛሽ መፍቱሀ ጋር አብራችሁ መጥታችሁ ችብስ ትወጅ የለ እንዴ ልጋብዛችሁ አለኝ
...እንደዚህ ሲለኝ የዶክተር ሷሊህ ትዝታ አእምሮየ ላይ ብልጭ አለብኝ
እሺ መልሼ እደዉልልሀለሁ ብየ ስልኩን ዘጋሁት..

ካሊድ ችብስ ልጋብዝሽ ያለኝ ችብስ በጣም እንደምወድ ስለሚያቅ ነዉ፡፡ አፓረንት ገጠር በወጣንበት ጊዜ ለራሱ ሲመጣ ይዞልኝ ይመጣ ነበር
..... .....ደዉየ መፍቱሀን ሳማክራት ምን ችግር አለዉ የምንሄደዉ አብረን ነዉ  እንሄዳለን አለችኝ

መፍቱሀ ሁሌም ቢሆን ካሊድ ጋር እንድቀራረብ ጥረት ታደርጋለች...ለኔ ጥሩ ነገር ነዉ የምታስብልኝ ..ሁሌም ቢሆን ሚፍታህ ጋር በምናወራ ጊዜ መፍቱሀ እንዲህ ትለኛለች....#ሚፍታህ_የጀመረሽ_ትዳር_ፈልጎ_ሳይሆን_ጓደኛዉ_አንቺን_ዳረኝ_ስላለዉ_አንቺን_ለማግባት_እልክ_ይዞት_ነዉ፡፡ ብላኝ ነበር ፡፡ መፍቱሀ እዉነቷን ነዉ...ብዙ ጊዜ ሚፍታህ ጋር የነበረንን ግንኙነት አልወደደችዉም ግን በፍቅር መሀል ጣልቃ አልገባም ብላ ትታን ነዉ፡፡ በፊት ጀምራ ታያለሽ አንቺ የካሊድ ነሽ እሱ ነዉ ባልሽ  ፡፡ አንቺን የሚወድሽን የሚጠቅምሽን እኔ ነኝ የማቀዉ ትለኛለች.... እኔ ግን ካሊድ ጋር ትዳር የማይታሰብ ነዉ ፡፡ ግን ለኔ በዚህ ጭንቀቴ መፍቱሀን የመሰለች ጓደኛ ፈጣሪ ባይሰጠኝ ምን ይዉጠኝ ነበር??? ፡
  ካሊድ ደዉሎ ግብዣየን ተቀበልሽኝ ወይስ አልተቀበልሽኝም?? አለኝ
.....እኔም እሺ ተቀብያለሁ አልኩት
.....ካሊድ በጣም ደስ አለዉ

የማይደርስ የለም የሀሙስ ለሊት ለጁምአ ቀን አስረከበች ከዛም ከኡስር ቡሀላ ካሊድ መኪናዉን ይዞ እኔ እና መፍቱሀን ይዞን ሊጋብዘን ጉዞ ጀመርን....እየሄድን ማንም የሌለበት ሰዉ የማይበዛበት ቦታ ዉስጄ ልጋብዛችሁ አለኝ
.....እኛም እሺ አልነዉ

ከዛም እልም ያለ ገጠር ዉስጥ ዛፍ አዋፋት የበዛበት ማንም ሰዉ የሌለበት ቦታ ወሰደን፡፡ ከመኪናዉ ወረድን ተቀመጥን ....ያለነዉ ሶስታችን ነን ወሬ ማዉራቱን ተያያዝነዉ...

በወሬያችን መሀል ካሊድ  እንደዚህ አለን......መፍቱሀ...እኔን ነዋል ብዙ ነገር በድላኛለች ..እሷ የበደለችኝን ነገር እሷ ባለችበት ለአንቺ ልንገርሽ እና ቅጣት እንድትቀጣልኝ እፈልጋለሁ አለ..
መፍቱሀም እሺ ተናገር አለችዉ
.....እኔም ካሊድ አንተን በድየህ አስቀይሜህ አቃለሁ እንዴ ???አልኩት
....አዎ ብዙ በድለሽኛል ነዋል አለኝ
....ምን ምን በድየሀለሁ ?? አልኩት

እሱም እንደዚህ አለኝ>>>>>>በሒወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ለትዳር ስጠይቅሽ አልፈልግህም አንተን ማግባት አልፈልግም ስትይኝ ለሁለት ወር ያህል አሞኝ ስራ መስራት አልቻልኩም ነበር አለኝ<<<<<
.....እኔም መታመምህን   በምን አቃለሁ??? አልኩት