Get Mystery Box with random crypto!

ሚፍታህ አላማዉ እኔን ማዉራት የጀመረዉ ለየሱፍ እኔን ድሮኝ ...እኔ ደግሞ ብዙ ጓደኞች ስላሉኝ ከ | ISLAMIC SCHOOL

ሚፍታህ አላማዉ እኔን ማዉራት የጀመረዉ ለየሱፍ እኔን ድሮኝ ...እኔ ደግሞ ብዙ ጓደኞች ስላሉኝ ከእነሱ መካከል አንዷን እኔዉ መርጬ እንድድረዉ ይመስለኛል ......ወይም አይታወቅም የሰዉ አስተሳሰቡ በየሱፍ አሳቦ እኔን የሱ ማረግ ፈልጎም ሊሆን ይችላል.....
  በመነገታዉ ሚፍታህ ደዉሎልኝ ለየሱፍ ነዋል አልተስማማችም ከአቅሜ በላይ ነዉ ብየ በስልክ ነግሬዋለሁ አለኝ.... ነገር ግን እኔና ሚፍታህ አሁንም ማዉራት አላቆምንም...እንደዉም ከበፊቱ በባሰ መልኩ እያወራን ነዉ፡፡

   ደግሞ በተዘዋዋሪ ካሊድ  ከኔ ተስፋ አልቆረጠም ሁሌም ጅንጀና አይሆንለትም....ካሊድ ግልፁን እንደሚወደኝ እና ለወደፊት እኔን ማግባት እንደሚፈልግ ይነግረኛል....ሁሌም ጁምአ እየደወለ ነዋል ተረጂኝ እኔ ጅንጀና አይሆንልኝም  .... ነዋል አንድ ጥያቄ መልሽልኝ ምን አይነት ባል ነዉ የምፈልገዉ ??? አለኝ

.......እኔም ብዙ ሴቶች ሲጠየቁ የሚመልሱትን መልስ መለስኩለት_እኔ የምፈልገዉማ የተማረ ዲን ያለዉ ኪታብ የቀራ ከምንም በላይ  የሚወደኝ የምወደዉ የሚሳሳልኝ ልጅ ወልደን በፍቅር አብረን መኖር የምንችል እና ""እስከ ማንነቴ የሚቀበለኝ"" አልኩት....
.....ካሊድም:- ነዋል አንድ ነገር ልታዉቂ እፈልጋለሁ >>>>>አንቺ የሆንሽዉን ብትሆኝ ሁለት ጊዜ ባል አግብተሽ ብፈቺ አምስት ልጅ ቢኖርሽ ለኔ ምንም አይደል...እኔ የምፈልገዉ አንቺ የኔ እንድትሆኝ ብቻ ነዉ የምፈልገዉ<<<<<< አለኝ
....ካሊድ እኔን ከማንነቴ የሚቀበለኝ ይመስለኛል...ነገር ግን በጭራሽ ዉስጤ ሊቀበለዉ አልቻለም .....ከካሊድ ጋር ከብዙ ንትርክ ቡሀላ  ከእኔ ተስፋ አልቆርጥ ሲል በዉሸት እኔ የዉጭ ሀገር ፕሮሰስ ጀምሪያለሁ አሁን ማግባት አልችልም ብየ በዉሸት ተስፋ አስቆረጥኩት....
....ካሊድም ሳይወድ በግዱ እሺ አለኝ ግን ያዉ ስለትዳር ባናወራም ጁምአ ጁምአ ይደዉልልኛል

በተዘዋዋሪ ደግሞ ሚፍታህ ጋር ሳወራ ደስታየ ነዉ ምነዉ እወድሻለሁ ላግባሽ ባለኝ እያልኩ እነዚህን ቃላቶች ቢነግረኝ ምኞቴ ነዉ
እንደዚህ እያለ የኮሌጅ አንደኛ አመት እና ክረምቱም በዚሁ  አለፈ ....ሁለተኛ አመት የኮሌጅ ትምህርት ጀመርን አሁንም ከአህመድ ጋር እያወራን ነዉ፡፡

አንድ ቀን እንዲህ አለኝ...>>>>ነዋል ማግባት እፈልጋለሁ የአሁኑ አመት ላይ የመጀመሪያ እቅዴ ማግባት ነዉ ለኔ የምትሆነዉን ምረጭልኝ<<<<አለኝ
......እኔም ምን አይነት ሴት ነዉ የምፈልገዉ ?? ከጓደኞቼ በመስፈርትህ መሰረት መርጬ ፎቶ እና ስልኳን ልኬልህ ከተግባባችሁ ትጋባላችሁ ግን መስፈርትህ ምንድን ነዉ?? አልኩት

.....እሱም እሺ መስፈርቴ ቁመቷ ልክ እንደ አንቺ.. መልኳ ልክ እንደ አንቺ.. የትምህርት ደረጃዋ. ዲኗ እድሜዋ..ልክ እንደ አንቺ ሁሉ ነገሯ ልክ እንደ አንቺ አለኝ፡፡
ግን ልክ እንደ አንቺ ማለቱ ምን ማለቱ ነዉ .......,,እኔም ሚፍታህን እየወደድኩት እሱን ማጣት ሳልፈልግ ሂጄ መፍቱሀን ለሚፍታህ ልዳርሽ አልኳት
......መፍቱሀም እኔ አልፈልግም አለችኝ...እሷም እኔ እንደምወደዉ ከአነጋገሬ ከሁኔታየ ተረድታኛለች ግን ነዋል ለምን ሚስት ፈልጊልኝ ከሚልሽ ለምን አንቺን አያገባሽም ??? እንዲህ የሚልሽ አንቺ አግባኝ እንድትይዉ...የአንቺን  ቃልሽን እየጠበቀ ይሆናል አለችኝ....
ወደዳችሁም ጠላችሁም ሚፍታህ በስልክ በተደጋጋሚም ስለምናወራ ልቤ ተሰርቋል አጉል መቀራረብ ፍቅር የሚባል ጦስ ይዞ ይመጣል..

የበፊት ያለፉት ምርጥ ትዉልዶች ፍቅርን እንዴት ነበር የገለፁት እስኪ ከዚህ የንጉስ የፍቅር አገላለፅ እንመልከት
★★★ ሕንድን የከፈተዉ ሱልጣን ጋዛሊን ማህሙድ በጣም ተወዳጅ የሆነ አገልጋይ ነበረዉ...ስሙ ሙሀሙድ ይባላል ሱልጣን ማህሙድ አገልጋዩን የሚጠራዉ ሙሀመድ በሚለዉ መጠሪያዉ ሲሆን አንድ ቀን ግን በአባቱ ስም ጠራዉ
..በዚህ የሱልጣኑ ድርጊት ልቡ የተሰበረዉ አገልጋዩ ሱልጣኑ ለምን በአባቱ ስም እንደጠራዉ ሲጠይቀዉ
>>>>>>>>የምወድህ ልጄ!! ሁልጊዜም በስምህ ስጠራህ ነዉ የኖርኩት .. #በእነዚህ_ጊዚያት_ሁሉ_ዉዱዕ_እያለኝ_ነበር የጠራሁህ...ሆኖም ግን አሁን በአባትህ ስም በጠራሁህ ቅፅበት ዉዱዕ አልነበረኝም..ዉዱዕ ሳላደርግ ይሄን የተባረከ ስም ሙሀመድን መጥራት ስላሳፈረኝ ነዉ በአባትህ ስም የጠራሁህ በማለት ይቅርታ ጠየቀዉ፡፡


ይሄን ያህል ለተወዳጁ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ፍቅር ነበራቸዉ ዉዱእ ሳይኖራቸዉ የተከበረ ስማቸዉን ለመጥራት ለራሱ ይሄን ያህል ፍቅራቸዉ በልባቸዉ ገብቶ ያከብራቸዉ ይወዳቸዉ ነበር...ዛሬ ግን ስማቸዉን በቀላሉ አንስተን ከልብ ባልመነጨ ፍቅር በነሽዳ በተራ ሙነሺዶች ...በተራ የሰርግ ነሽዳ አድማቂ ተብየ ወጣቶች በዱአዉ በነሽዳዉ ሙሀመድ ነብየ ስንል እንዉላለን ሁሉም ከአንገት በላይ ነዉ..እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ የነብዩን ልጆች ሁሉንም በቃላችን ሸምድደናል??ነብዩ በስንት አመታቸዉ ነዉ ነብይ የሆኑት??የነብዩ ሚስቶች ጥቀሱ ብትባሉ ስንቱን መጥቀስ እንችላለን?? ከነብዩ ምርጥ ሱሀቦች ስንት እናዉቃለን?? በስንት አመተ ሂጅራ ተወለዱ ?? ወዘተ የተለያዩ ጥያቄዎችን እራሳችንን እንፈትሽ፡፡ አሁን ላይ ገና እንቦቅላ ወጣት ተነስቶ ነሽዳ አወጣሁ ብሎ ሙሀመድ ነብየ ሲል ይስታወላል..ሰዉ በተዉሂድ መተናፅ ሲገበረዉ ሙነሺድ ተብየዎች ሰዉን ለማዘናጋት በቃል ብቻ የቀረ ከሆድ ያልገባ ዉዴታ ነቢይ ነቢይ እወድወታለሁ እያሉ ነሽዳ ሲያወጡ አብረዉ ሽርካ ሽርኩን ጨምረዉ ህዝቡን በጭፍን ሲመሩት እያየን ነዉ ...ግን የነብዩ ዉዴታ ይሄ ነዉ?? በፊት የነበሩ ምርጥ ትዉልዶች ግን ሙሀመድ የሚለዉን ስም ዉዱዕ ሳይኖራቸዉ ለመጥራት ይከብዳቸዉ ነበር እኛ ግን አብሮ ቂጣ እንደበላ ጓደኛ ስማቸዉን ስናነሳ እንደ ጩጫን እንኳ ክብደት አልቆጠርንም ...??እኛ ዉዴታን የምንገልፀዉ የማይጠቅም ግን ብዙ የሚጎዳ ነሽዳ እያዳመጡ አብሮ ሙሀመድ ነብየ ማለት ነዉ ?? ዉዴታ በነሽዳ ነዉ የሚገለፀዉ ??
ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ እኔን የሚወደኝ የሰራሁትን ስራ ይከተል ብለዋል...ዉዴታ የሚገለፀዉ እሳቸዉ የሰሩትን ስራ በመስራት ነዉ... መቼ ነዉ ሁላችንም ከኔ ጀምሮ ተዉሂድ ለመማር ፍቃደኛ የምንሆነዉ??ተዉሂድን ተምረን ትክክለኛ የእሳቸዉን መንገድ ተከትለን የእሳቸዉን መዉደዳችን የምናረጋግጠዉ?? ሁሉም መልሱን በልቡ ይመልስ....
   

ሚፍታህ ጋር  ማዉራቱን ተያይዘንዋል.... ረመዷን ደርሷል ፡፡ በዛዉም coc ፈተና ስለነበረኝ እየተዘጋጀሁ ነዉ፡፡

በጊዜ ሒደት አንድ ቀን እንዲህ አለኝ ነዋል ለየሱፍ ቢያወራሽ በጭራሽ እንዳነግሪዉ አደራ :-እኔ ለየሱፍ ልድርሽ ነበር ያሰብኩት .... ምርጫሽ እሱ ካልሆነ ካልፈለግሽዉ እኔ ላገባሽ እፈልጋለሁ ነዋል ወላሂ ከምሬ ነዉ አንቺን ማዉራት ከጀምርኩ ቡሀላ ወላሂ በልቤ ገብተሻል እወድሻለሁ አለኝ.....

 
#ክፍል
ይ...........ቀ............
.......ጥ...........ላ..........ል

Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group