Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ስድስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ገና በመጀመሪያ በደወለልኝ ቀን የሆነ መግለፅ የማልችለዉ ብዥታ አእምሮየን አናወዘዉ...ይገርማል


ማታም ልተኛ ስል ደወለልኝ እያወራን ነዉ........ቀን በቀን ቀን ማታም መደዋወሉን ከሚፍታህ ጋር ተያይዘንዋል ለምን በፊት ስለምንግባባ ለማዉራት እሱም እኔም አንፈራራም ፡፡ በቀላሉ እንደ ሴት ጓደኛ እንደምናወራዉ ያህል የእኔ እና የሚፍታህ ቅርርብ ወሬ እንደዛ ሆነ.........

አንዴ በስልክ እያወራን ነዋል ትልቅ ሰዉ ሁነሻል አሉ ፎቶሽን አሳይተዉኝ እኔ የማቅሽ ልጅ እንደነበርሽ ስለሆነ ነዋል አይደለችም እስከማለት ደርሼ ነበር በግድ አመንኩኝ... የሇላዉ መጣ እና የፊቱን ቀደመዉ እኛ እናሳድጋለን በቃ እናንተ ግን ያሳደጋችሁን ትረሳላችሁ ብሎ አሳቀኝ
...,ኪታብ ምን እንደምቀራ ጠየቀኝ ነገርኩት
....,እሱን ስጠይቀዉ አዲስ አበባ ነዉ የምኖረዉ ፡፡
ትምህርትም የተማርኩት አዲስ አበባ አዉልያ ኢስላማዊ ትምህርት ቤት እና ቁርአን የሀፈዝኩትም አዲስ አበባ ነዉ፡፡ አሁን የምሰራዉ ከቻይና ከዱባይ እቃ እያመጣሁ አዲስ አበባ ማከፋፈል ነዉ አስመጭ እና ላኪ ሁኜልሻለሁ አለኝ፡፡ ...አልሀምዱሊላህ ሒወት መስመር ይዛልኛለች ግን አንድ ነገር ብቻ ጎዶሎ ሁኖብኝ ያለኝ ብር ንብረት ደስታ አልሰጠኝም ጎዶሎ እንደሆንኩ ይሰማኛል አለኝ
.......እኔም ምንድን ነዉ የጎደለህ?? አልኩት
.........,እሱም ትዳር የለኝም ማግባት እፈልጋለሁ ...ደግሞ የማገባዉ.አንቺ የመረጥሽልኝ ከጀመአ ልጆች  ነዉ የምፈልገዉ ፈልጊልኝ  አለኝ
.....እኔም አብሽር ጣጣ የለም አንድ ላይ ሁነን እንፈልጋለን አልኩት፡፡
ግን ትዳር በፍለጋ ይገኝ ሁን ?ትዳር ቀልድ ነዉን?በኔ ፍለጋና በሚፍታህ ሀሳብ ይሳካ ይሆን?ለምን ትዳር በባህሪዉ መረጋጋት ትዕግስት ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
★★★ትዳር በባህሪው ትግዕስትን ይፈልጋል ኢማንና ፍቅርን አላማቸው አድርገው ባንድላይ ለመሆን የወሰኑ ሰዎች መደማመጥን ሀሳብን መቀባበል ካልቻሉ በዘመናችን ከእሾህ እንደተጠጋ ቁልቋል ሲያለቅሱና ሲያማርሩ እንዲሁም ደስታና ሰላም የሸሸው ህይወትን ሲገፉ ይኖራሉ።

   ዛሬ ዛሬ አያሌ የዘመኑ ወጣቶች ትዳርን አስበውበትና ወስነው ሳይሆን በዘፈቀደ ለጊዜያዊ ስሜት ብለው የሚገቡበት መሆኑ በጉልህ የሚታይ ነው ጋብቻ እርቆ ማሰብና ማሰላሰልን ብሎም መወሰንን ይጠይቃል።

ይሁንና ጋብቻ ሲጀመር ብዙ ውጣ ውረድ እንዳለው የሚዘነጉ ቀደም ብሎው ያላሰቡበት አንዳንዶች ገና ከጅምሩ በጋብቻቸው የተደላደለ ኑሮን ለመኖር ይፈልጋሉ፡፡ የትዳርን ትክክለኛ ገፅታ ማየት ተስኗቸው ትዳርን በየዋህነት የሚጀምሩ ሰዎች ትዳር እንዳሰቡት ሳይሆን ሲቀር ያለው አማራጭ የያዘውን ትቶ ሌላ ለመሞከር እንድ ሁለት ማለት ይሆናል ፡፡በመሆኑም ፍቅርንና ኢማንን አላማቸው አድርገው በትዳር ተሳስረው ለመኖር የወሰኑ ሰዎች በሰርጋቸው ማግስት ወይም በቀጣዩ የትዳር ህይወታቸው ውስጥ ግራ የሚያጋቡና ተስፋ የሚያስቆርጡ የስሜት አለመጣጣም የፋላጉት አለመርካት የአመለካከትና የልምድ ማነስ ልዩነቶች የሚታይበት ሊሆን ይችላል።

#ይሁን_እንጂ ትዳራቸውን እንደ አላህ ፍላጎትና ትዕዛዝ የጀመሩ ከመሆናቸው የተነሳ ለጊዜያዊ ችግር ብለው ወደ ፍቺ (ትዳርማፍረስ) አይሮጡም፡፡ ከዚህ ይልቅ ለገጠማቸው ችግር አላህ ሱበሀን ወተአላ ከልብ እየተማፀኑና የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ አብረው ይሞክራሉ .... አንዱ የሌላውን ሃሳብ ለመቀበልና የታየውን ድክመት በይቅርታ ለማለፍ ፍቃደኞች ይሆናሉ። ይህም ትዳራቸው አስደሳች ህይወትና ረጅም ዕድሜ እንዲኖረው ለማድረግ ከማንም የተሻለ ዕድል ይሰጣቸዋል። ጋብቻ የተከበረ የህብረተሰብ የመጀመሪያ ተቋም እንደመሆኑ መጠን

ይህ ተቋም ያማረና የተስተካከለ እንዲሆን የአላህ
እዳርታ የግድ ስለሚሆን አላህ ሱበሀን ወተዓላ መለመንና መማፀን ያፈልጋል።አላህም በቁርአኑ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል

«ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፡፡ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን» የሚሉት ናቸው፡፡

በዚህ መልኩ የትዳር ህይወትን ከጀመሩ በኋላ ስለአንድነታቸውና ፍቅራቸው በጋራ ዱዓ በማድረግ መትጋት ይኖርባቸዋል ስለትዳራቸው በግልፅና በታማኝነት አብሮ መወያየትና መነጋገር ከቻሉ ዓላማቸው የሚሰምር መሆኑን ተስፋ እናደርጋለን የሚያጋጥሟቸው ችግሮችም በአላህ ሱበሀን ወተዓላ ፊቃድ ይወገዳሉ። ፈጣሪ ሚፍታህ ያሰበዉን አይነት ትዳር ለኔም የተፃፈልኝን አሳካልን ብየ በዱአ ተያይዣለሁ ፈጣሪ ይገዝሽ በሉኝ


      ሚፍታህ ከበፊቱ በበለጠ እያወራን ነዉ ማርሽ መጨመር እንጂ መቀነስ አይታሰብም ፡፡
ሚፍታህን ዲነኛ አዋቂ አድርጌ ነዉ የማስበዉ..ለምን ቁርአን ሀፊዝ ነዉ በተጨማሪም አዉልያ ኢስላማዊ ትምህርት ቤት ነዉ የተማረዉ በቂርአቱም በዲኑም በትምህርቱም ጎበዝ ስለሆነ ምነዉ ለኔ በሆነ ብየ ተመኘሁ፡፡፡

አንድ ቀን ሚፍታህ እንደዚህ አለኝ የአንቺን ስልክ ቁጥር የሰጠኝ የሱፍ ነዉ ነዋልን አዉራልኝ ብሎኝ ነዉ አለኝ...
.....እንዴ የሱፍ ጋር ትግባባላችሁ እንዴ ??? አልኩት
......,እሱም አዎ አንድ ነገር ልንገርሽ እኔ አንቺን የማወራሽ የሱፍን በfb አላወራዉ ስላልሽዉ ነዉ በጣም ነዉ የሚወድሽ ሁሌም ስንደዋወል ነዋል እወዳታለሁ እባክህ አንተ የኡስታዝ ልጅ ስለሆንክ፡በፊት ትግባባላችሁ ....አሁንም አንተ የምትላትን ስለምትሰማ በዛ በዚህ ብለህ አሳምንልኝ ብሎ ስልክሽን ሰጥቶኝ ነዉ አለኝ......
.......ጉድ ነዉ በጣም አጀበኝ ...የሱፍ ማለት እዚሁ ጂማ የሚኖር ጎረቤታችን ነዉ፡፡ የሱፍ ብዙ ጊዜ Facebook ላይ ያወራኛል እኔ ግን ከ10ክፍል ቡሀላ fb ላይ ማዉራት አይመቸኝም.... እሱ ቢያወራኝም ለማዉራት ቢፈልግም እኔ ግን አላወራዉም ፡፡

የሱፍ የሰራዉ ስራ በጣም አናደደደኝ እኔን ከፈለገኝ እኔን ከወደደኝ እኔን ማግባት ከፈለገ ፍቅር እና ትዳር ሰዉ የሚገባበት ወይ እኔ እምቢ ስል ነዉ እንጂ የሱፍ እኔን ማግባት እየፈለገ እንዴት ለሚፍታህ ነዋልን የወደፊት ሚስቴ እንድትሆን አመቻችልኝ ይላል ???? በጭራሽ የማይደረግ ነዉ የሰዉ ልጅ መጀመሪያ ግልፁን መናገር ነዉ እንጂ በታዋቂ ሰዉ ወይም በታዋቂ ሰዉ ልጅ እንደዚህ አይነት ስራ መስራቱ በእኔ አስተሳሰብ የወረደ እና በጣም የሚያሳፍር አስተሳሰብ ነዉ፡፡
እኔም ያወራኝ ለራሱ አለመሆኑን ሳዉቅ ከሚፍታህ ተስፋ ቆረኩ ....እኔም አሁን ላይ አላገባም መማር ነዉ የምፈልገዉ....  እናም አደራ የሱፍን እንደማልፈልገዉ መቼም እንደማላገባዉ ከኔ ተስፋ እንዲቆርጥ ንገረዉ አልኩት፡፡
....ሚፍታህም እሺ ካልፈለግሽ እምቢ ብላለች አልተሳካም ብየ እነግረዋለሁ አለኝ፡፡

ሚፍታህ ለሌላ ልዳርሽ ከሚለኝ እኔ ላግባሽ ቢለኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር....ምን ይደረጋል ነበር ሁኖ ቀረ፡፡ አንድ ነገር ይገርመኛል ሴት ልጅ የምትወደዉን ስትከተል የሚወዳትን ታጣለች ይባላል ካሊድ ላግባሽ ብሎ ስንት እንዳለመነኝ እኔም እምቢ እንዳላልኩኝ ..ግን ሚፍታህ ገና ለወደፊቱ ላግባሽ ቢለኝ ደስታየ ነዉ ምንም ሳላቅማማ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ