Get Mystery Box with random crypto!

ካሊድ ለሰልዋ እኔን እንደሚወደኝ ለወሬ ለጅንጀና ሳይሆን ቀጥታ ሽማግሌ ልኬ ማግባት ነዉ የምፈልገዉ | ISLAMIC SCHOOL

ካሊድ ለሰልዋ እኔን እንደሚወደኝ ለወሬ ለጅንጀና ሳይሆን ቀጥታ ሽማግሌ ልኬ ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ብሎ ነግሯታል
....ሰልዋ እኔን ስጠይቀኝ እኔ አሁን ማግባት አልፈልግም ቤተሰብም እንድማር ነዉ የሚፈልጉት አልኳት
........ከአሁን በፊት ካሊድ ብዙ ቀን ለሰልዋ እና ለመፍቱሀ እኔን እንደሚወደኝ ነግሯቸዋል፡፡ ካሊድ እኔን ለማዉራት በጣም ይፈራኛል ..ስለእኔ ጉዳይ የሚጠይቃቸዉ ሰልዋን እና መፍቱሀን ነዉ፡፡ለትዳር ዝግጁ ከሆነች እኔን ማግባት ምርጫዋ ከሆነ ዛሬ ነገ ሳልል ሽማግሌ ልኬ ለማግባት ነዉ አላማየ እያለ ሁሌ ይነግራቸዋል፡፡

ካሊድን ባንግባባም አቀዋለሁ ባጃጅ አለዉ በኛ አካባቢ መስመር ነዉ የሚሰራዉ ፡፡ ግን በእሱ ባጃጅ ስሄድ ትኩር ብሎ ያየኛል
......ሰልዋ ቀን በቀን ካሊድን ምን አሰብሽ?? አግቢዉ እያለች ስትጠይቀኝ ካሊድ ከኔ ተስፋ እንዲቆርጥ ብየ.....ማግባት አልፈልግም ስለዚህ ጉዳይ ሁለተኛ እንዳታነሺ አልኳት

እሺ ነዋል ግን ስልክ ቁጥሯን ስጭኝ ብሎኛል እሰጠዋለሁኝ አለችኝ
....እኔም እሺ ስጭዉ የተለየ ነገር ግን አይፈጠርም አልኳት

ካሊድ ጋር የምናወራዉ በTelegram ነዉ በስልክ እኔን ለማዉራት ድምፄን ለመስማት ይፈራል
በTelegram እያወራን እኔን ማግባት እንደሚፈልግ በግልፅ ነገረኝ
........እኔም ካሊድ ተረዳኝ አሁን ማግባት አልፈልግም ትምህርቴን መማር ነዉ የምፈልገዉ ከአሁን ቡሀላ ስለትዳር እንዳታነሳብኝ ብየ ተቆጣሁት
.....ነዋል ትምህርት እኮ ከትዳር አይከለክልም አለኝ
....,ከዛ በቃ አልፈልግም ተወኝ ብየ ከtelegram ወጣሁኝ፡፡ ተነስቼ ዉዱእ አድርጌ ሶላተል ኢስቲሀራ ሰገድኩኝ ..ልክ እንደሰገድኩኝ ልቤን እፍን አደረገኝ መረጋጋት አልቻልኩም...,ወዳዉ ለካሊድ በmessage መልዕክት ላኩለት

መልዕክቱም እንዲህ ብየ ነበር የላኩለት
"""""ካሊድ ሶላተል ኢስቲሀራ ስሰግድ ልቤን አፈነኝ የሰላም ስሜት አልተሰማኝም  ስለዚህ ተረዳኝ እኔ በጭሬሽ አንተን ላገባህ አልቾልም የትዳር ምርጫየም አይደለህም አልፈልግህም""""" አልኩት
......ካሊድም የላኩለትን message አይቶት---- መልሶ እንደዚህ ብሎ ላከልኝ-------ነዋል አብሽሪ አንቺን እየጀነጀንኩሽ አይደለም ደግሞም በኔ የተነሳ እንድትጨናነቂ እንድታስቢ አልፈልግም  ፡፡ ባይሆን አንድ ነገር ብቻ ፍቀጅልኝ በሳምንት አንድ ቀን ለሰላምታ ስደዉልልሽ አንስተሽ ፈታ ብለሽ አዉሪኝ መንገድም ላይ ስንገናኝ ሰላምታ ሳቀርብልሽ ፊት እንዳነሽኝ አናግሪኝ አለኝ
....,,እኔም እሺ በዚህ እስማማለሁ አልኩት

ከካሊድ ጋር በTelegram ማዉራት ቀነስን ሁሌ በሳምንት ጁምአ ጁምአ 8:00 ሰአት ሲል ሁሌ ይደዉልልኛል ፡...ከዛም እንዴት ነሽ ቤተሰብ ሰላምናቸዉ ??ጁምአ እንዴት ነበር ?? ትምህርት እንዴት ነዉ ?? ሳምንቱ እንዴት አለፈ ብሎ ይጠይቀኛል...
....,አጠር አጠር አድርጌ እመልስለታለሁ ከ10ደቂቃ የበለጠ ሳናወራ በአጭሩ ቶሎ ወሬያችንን እንጨርሳለን ፡፡ ሁሌ ጁምአ Alarm የቀጠረ ይመስለኛል 8:00 ሲል ይደዉልልኛል ከዚህ ዉጭ ከካሊድ ጋር ሌላ በስልክ ቅርርብ የለንም

  አንድ ቀን ክላስ በነበርኩበት  ቲወሪ የተማርነዉን ፕራክቲክ የምንሰራበት የምናይበት ክፍል(Dimonstration class) ሁኜ በፕራክቲክ እየተማርን .....የማለቀዉ ስልክ ቁጥር ተደወለ
.....,እኔም ማንሳት ስላልተመቸኝ ማንሳቱን ተዉኩት
..........አሁንም በድጋሜ ተደወለልኝ ፡፡ አሁን ድረስ የሚገርመኝ ስልኩ ሲደወል ጭንቅ ጥብብ አለኝ ሳየዉ ስልኩ አስፈራኝ....ይሄ የማላቀዉ ቁጥር ማን ይሆን ????
.... እየተደወለ ሲደጋገም መምህሬን አስፈቅጄ ወደ ዉጭ ወጥቼ ስልኩን አነሳሁት........



ነዋል አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ አለኝ
...እኔም ወአለይኩም ሰላም ወራህመቷሏሂ ወበረካትሁ አልኩት
....ሰላም ነሽ እንዴት ነሽ ነዋል?? አለኝ
........አልሀምዱሊላህ
......አወቅሽኝ ??? አለኝ
....እኔም አረ አላወኩህም ማን ልበል ??
......እሱም እርግጠኛ ነሽ አላወቅሽኝም ??ይሄን ድምፄን አስታዉሺ አለኝ
......እኔም በጭራሽ ይሄን ድምፅ ላስታዉሰዉ አልቻልኩም
.....እሱም እርግጠኛ ነሽ ??
..........እኔም አዎ እርግጠኛ ነኝ
.....ማስታወስ ባለመቻልሽ ገርመሽኛል ለማንኛዉም ሚፍታህ እባላለሁ አለኝ
..... አሁንም ላስታዉስህ አልቻልኩም አልኩት
....እሱም እንዴት ???
........ብዙ ሚፍታህ የሚባሉ ሰዎችን ስለማወቅ ልለይህ አልቻልኩም
............እሺ ከእነዚህ ብዙ ሚፍታህ ስሞች ዉስጥ የማትረሺዉ የትኛዉን ነዉ ???
.....በጣም አናደደኝ ሰማሀኝ ወንድም ለጅንጀና ጊዜም ሰአትም የለኝም ተወት አድርገኝ ብየ ተቆጣሁት
.....,አትቆጪ ሲርየስ አትሁኝ ሲርየስ መሆን ለወታደር ነዉ ለዛዉም ግድ ሁኖበት ነዉ...ለማንኛዉም አሁን ክላስ ነሽ መሰለኝ ቡሀላ ደዉየ ማንነቴን በደንብ እነግርሻለሁ አለኝ
...... እሺ ብየ ስልኩን ዘጋሁት
     
ስልኩን አዉርቼ እንደጨረስኩ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ከየት እንደመጣ የማላቀዉ ተሰማኝ ..ገና ማንነቱን ሳላዉቀዉ ደዉሎ ለስለስ ባሉ በሚያምር ድምፆቹ ስላወራኝ ብቻ ደስተኛ ሁኛለሁ ...አላህ ለኸይር ያርግልኝ ....ከዛም ወደ ፕራክቲክ ክላስ ገባሁኝ፡፡

    ከትምህርት ቤት እንደወጣሁ አሁንም ቅድም በተደወለበት ስልክ ቁጥር ተደወለልኝ ....እኔም አነሳሁት ፡፡ እንደቅድሙ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.....,አሁንስ አስታወሽኝ ??? አለኝ
......... አላስታወስኩህም አልኩት
......እሺ ካላስታወሽኝ አላህ ቀልቡን እስኪ ሰጥሽ ማንነቴን ልንገርሽ ... አንቺን ኪታብ የሚያቀሩሽ የኡስታዝ ልጅ ነኝ አሁንስ አወቅሽኝ ???አለኝ
ሚፍታህን አሁን አወኩት የተለያየ ኪታብ ያቀሩን የኡስታዛችን ልጅ ነዉ
......... አዎ አዉቄሀለሁ አልኩት
......የተለያየ ወሬ ካወራን ቡሀላ ነዋል ከአሁን ቡሀላ እደዉልልሻለሁ ከአንቺ ትልቅ ሀጃ አለኝ ...ብሎ በአፉ ተነፈሰ
......እኔም እሺ ብየ ቻዉ ተባብለን የስልክ ወሬያችንን ጨረስን
.......ሚፍታህ የኡስታዛችን ልጅ ነዉ፡፡ በፊት ኪታብ ስቀራ ይቆጣጠረኛል፡፡ .... ወንድ ጋር ካወራሁ ይመክረኛል ...የሴት መጥፎ ጓደኞች ስይዝ ተይ እነዚህ ዱርየ ናቸዉ አይጠቅሙሽም ይለኛል፡፡ ኪታብ እየሰጠኝ ቅሪ እያለ ያበረታታኝ ነበር፡፡
ከዛ ወደ ዉጭ ሀገር ለስራ እንደሄደ ሰምቻለሁ ከአየሁት ብዙ አመታት አልፈዋል ....ዛሬ መደወሉ ገርሞኛል ደግም ከአንቺ ትልቅ ሀጃ አለኝ ብሎኛል እያልኩ ብቻየን እንደ እብድ አወራ ይዣለሁ፡፡ ገና በመጀመሪያ በደወለልኝ ቀን የሆነ መግለፅ የማልችለዉ ብዥታ አእምሮየን አናወዘዉ...ይገርማል


#ክፍል
ይ........ቀ.............
......ጥ........ላ................ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•