Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ አምስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ





አብራኝ መድረክ የምትመራ ሰልዋ የምትባል ጓደኛ ነበረችኝ ...እሷም ብዙ ሰዉ አንቺ እንድመሪ ይፈልጋሉ ..አንቺ አቅርቢ አስተያየት ላይ ነዋል መድረክ ትምራ እየተባለ ስለሆነ አንቺ ነሽ መምራት ያለብሽ ትለኛለች፡፡ ሰልዋ አግብታለች ሁሌ አብረን ስንሆን ትዳር እንዳገባ ትመክረኛለች ..ነዋል አንቺን ብዙ ሰዉ ዳሪኝ አስተዋዉቂኝ እያሉኝ ነዉ፡፡ ትዳር ምን ያህል ደስታ እንዳለዉ ትነግረኛለች፡፡ እኔ ያገባሁት ቤተሰብ ያመጡልኝን ነዉ እንጂ ከትዳር በፊት Boy frind ብየ የያዝኩት ማንም ወንድ የለም ..ቤተሰብ ለኔ ይሆናል ብለዉ መርጠዉ ያመጡልኝ ጋር ተጋብተን በጣም ተዋደን ተፋቅረን ልጅም ወልደን እየኖርን ነዉ፡፡ ለምን ብትይ ከትዳር በፊት እንጠናና እየተባባልን ስላልተሰላቸን ይሄዉ ፍቅር ሰጥቶኝ እኔም ሰጥቸዉ እየኖርን ነዉ ትለኛለች ሰልዋ የዘወትር ምክሯ ነዉ፡፡
ሰልዋ በምትመክረኝ ምክር ምነዉ በአገባሁ እያልኩ ጥሩ ትዳር መመኘት ጀመርኩኝ...

★★★★ ከኒካህ በፊት ስለማንነታችን በደንብ እንተዋወቅ። ለትዳር ሂወታችን ጠቃሚ ስለሆነ እየተጠናና እንቆይ የሚባለው አባባል ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል?
የሴት ልጅ ክብሯ እና ውበቷ እራሷን የህዝብ ሃብት ከማድረግ መቆጠብ መቻሏ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሂጃብ ከማደረግ እራሷን ከመሸፈን አንስቶ ከማንኛውም አይነት አጂ ነብይ ወንድ ጋር ከኒካህ በፊት ግንኙነት ሳታደርግ መቆየት መቻሏ ነው፡፡

ወጣቱም፣አዋቂውም፣ጃሂሉም ባጠቃላይ ማገናዘብ የጀመረ ሙስሊም በሙሉ ከኒካህ በፊት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ በኢስላም ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህን የአላህን ክልከላ አውቆ የሚርቀው ግን በጣም ጥቂቱ ነው፡፡

በኢስላም ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን መልካም የሆኑ ባል እና ሚስቶችን የሚጣመሩበት ይሆን ዘንድ ያዛል፡፡ ባለጌ ባለጌን እንጂ ጨዋን እንድታገባ በኢስላም አይፈቀደም፡፡ በዝሙት የተጨማለቀ ወንድም የሱ ቢጤውን እንጂ ጥብቅ የሆነችን ሴት እንዲያገባ አይፈቀደም፡፡ ታዲያ ከጋብቻ በፊት ዝሙት እስካልፈፀምን ድረስ ይህ ክልከላ አይመለከተንም ይባል ይሆናል፡፡

መረጃውም አላህ በተከበረ ቅዱስ ቁርአኑ እንዲህ ይለናል፡-
ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ አግቧቸው፡(ሱራ አል ኒሳዕ፡25) ብሎ አስቀምጦልናል፡፡

ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ይህን አንቀፅ  ሲፈስሩት ጥብቆች የሆኑ ማለቱ ምንም አይነት ዚና ያልፈፀሙ እና የብልግና ተግባር ከማንም ጋር ለመፈፀም እሺ የማይሉ እና ፍቅረኛ ያልያዙትን ማለት እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡

ተመሳሳይ መልዕክትም በሱረቱል ማዒዳ ላይ የሚከተለውን እናገኛለን

ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው፡፡(አል ማዒዳ፡5)

ይህንንም አንቀፅ አስመልክቶ ኢብኑ ከሲር(አላህ ይዘንላቸው) ሲያብራሩ ጥብቅ የሆነችን ሴት የሚለውን ከዝሙት የራቀች ፣የወንድ እጮኛ ያልየዘች መሆኑን በመግለፅ ይህ ድንጋጌ ወንዱም ጥብቅ፣ዝሙተኛ ያልሆነ፣የሴት እጮኛ ያልያዘ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ በዚሁ ማብራሪያቸው ላይ ብዙ እጮኛ ያለውም ሆነ አንዲት እጮኛ ተመሳሳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚህ ማብራሪያ ላይ ኢማሙ አህመድ(አላህ ይዘንላቸው) ከላይ በተገለፀው አንቀፅ መሰረት ጥብቅ ያልሆነ ወንድ ወይም እጮኛ የያዘ እንደሆነ ጥብቅ የሆነችን ሴት ተውበት አድርጎ ከድርጊቱ ሳይመለስ ማግባት ለሱ የተከለከለ መሆኑን ፡፡ እንዲሁም ጥብቅ ያልሆነች ሴት፣ ወይም ወንድ እጮኛ ይዛ የነበረች ሴት ከድርጊቷ ተውበት አድርጋ እስካልተመለሰች ድረስ ጥብቅ ወይም ጨዋ ወንድን ማግባት ክልክል ነው ማለታቸውን ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ላይ ገልፀዋል፡፡

እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው ሴት እጮኛም ሆነ የወንድ እጮኛ መያዝ ምን ያህል የተከለከለ መሆኑን በግልፅ ተቀምጦልናል፡፡

አብዛኞቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ እራሳችንን የምንሸውድባቸው መገለጫዎች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ይህን ሃራም የሆነ ፆታዊ ግንኙነት ሃላል ለማስመለስ ከምንጠቀማቸው ምክንያቶች መካከል. ፡- እኛ አላህ ለሚወደው የትዳር ሂወት ተሳሰብን እንጂ ለሀራም አልተፈላለግንም፣ በቅርቡ ኒካህ ለማሰር አስበናል፣ ትምህርቴን እስክጨርስ እንጂ ኒካህ ቶሎ እናስራለን፣ አንዳንድ ነገሮችን እስካስተካክል ድረስ እንጂ ሽማግሌ እልካለው፣ ቤተሰቦቼ ልጅ ነሽ ስለሚሉኝ ላይፈቅዱ ስለሚችሉ እነሱን እስካሳምናቸው ትንሽ ታገሰኝ፣ ለትዳራችን የሚሆን መኖሪያ ቤት እና ቁሳቁስ እስካሟላ ጠብቂኝ፣ በአካል እስካልተገናኘን እኮ ሀራም ላይ አንወድቅም፣ ሰው ባለበት አካባቢ ብቻ አብረን ስለምንሆን ችግር የለውም፣ ከኒካህ በፊት ስለማንነታችን በደንብ ማወቅ ለትዳር ሂወታችን ጠቃሚ በመሆኑ እየተጠናናን ነው፣ ወዘተ..የሚሉ እራስን መሸወጃ ምክንያቶችን በመስጠት በሀራም ግንኙነት ውስጥ መዘፈቁን ይቀጥላሉ..ስለሆነም በሀራም የተጀመረ ነገር በረካ ስለሌለዉ .ሁሉም ለአቅማ አዳም የደረሰ ሰዉ ትዳርና እንቅልፍ በራሱ ጊዜ ይመጣል ብሎ መሶበር ከሀራም መራቅ እና ለሌት እየተነሱ ቁርአን እየቀሩ ከሶላትም በፊትም ቡሀላም በዱአ መበረታታት አለበት፡፡ ትዳር ከፈጣሪ የሚሰጥ ፀጋ ነዉ እንጂ ከፈጣሪ ባይሆንማ በየመንገዱ ያላገባ ወንድም ሴትም መንገዱን ይመላለስበታል..ስንቱን ለትዳር እንመኛለን??ግን ብዙ ተመኘን የምናገባዉ ግን ፈጣሪ የመረጠልንን አንዱን(አንዷን) መሆኑን የማይካድ ሀቅ ነዉ፡፡


ወንድ ለብቻ ሴት ለብቻ በመጋረጃ ተጋርዶ ስንሆን እኛ ሴቶቹ ዝግጅት ስናዘጋጅ ዳቦ ተቆርሶ ወይም ዉሀ ለመስጠት ወደ ወንዶቹ ወደሚቀመጡበት ከመጋረጃ ጀርባ ላላዉ ስጪ ሒጂ አድርሺ ትለኛለች
.....እኔም አልወስድም ሌላ ሰዉ ላኪ እላታለሁ
.....ከዛም እንደዚህ ትለኛለች ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አሚሩን የተኻለፈ የረሱልን ትእዛዝ ኺላፍ ያደረገ ነዉ ደግሞ የረሱልን ኺላፍ ያደረገ ደግሞ አላህን ኺላፍ ያደረገ ነዉ ትለኛለች፡፡ እኔም ሳልወድ በግዴ ወደ ወንዶቹ መቀመጫ ሂጄ የላከችኝን የሚበላ የሚጠጣ ነገር ሰጥቼ ወዳዉ እወጣለሁ
ሰልዋ ማታ ትደዉልልኝ እና ስትገቢ እንደዚህ የለበሰዉ አንደዚህ ያለሽ ልጅ ብዙ ምልክት ትነግረኝ እና ልጁን ሳወቀዉ እሱ ልጅ ዳሪኝ እያለ ጠይቆኛል ትለኛለች...

ሰልዋም ምን ይሻለኛል?? ለየትኛዉ እንደምድርሽ የትኛዉን እንደምመርጥልሽ ግራ ገባኝ ዳሪኝ እያሉ ብዙ ሰዉ ጠየቀኝ ተቸገርኩኝ......ትለኛለች፡፡
..እኔም ቆይ እስኪ ልሰብበት ሰልዋ እላታለሁ

  .....እኔ የምፈልገዉ ከነማንነቴ የሚቀበለኝ ..በልጅነት መደፈሬን አዉቆ ሞራሌን የሚጠብቅልኝ ነዉ .... ደግሞ እሺ ተቀራረብኩኝ የኔን ማንነት እንዴት አድርጌ ነዉ የምነግረዉ ??? እንዴት ብየ ወንዶችን እቀርባለሁ??? እያልኩ ብቻየን በሀሳብ ጭልጥ ብየ ሀሳብ ወስዶ ይመልሰኛል

አንድ ቀን ሴት ተማሪዎች ቁርአን ሀፍዘዉ ስለጨረሱ ትልቅ ዝግጅት ተዘጋጅቷል ፡፡ አንድ ወጣት ጋር ስለዝግጅቱ ሰልዋ ጋር ያወራል... እኔ ስመጣ እንተዋወቅ አለኝ
.....እኔም እሺ አልኩት
.... ካሊድ እባላለሁ አለኝ
...እኔም ነዋል እባላለሁ አልኩት
በዛዉ ተዋዉቀን እናም አብረን እሷ ጋር ሄድን