Get Mystery Box with random crypto!

        መፍቱሀ ዓሊይ መስጂድ የሚገኘዉ የሴቶች ጀመአዉ ላይ አሚር ስለሆነች እኔ በተለለያዩ ነ | ISLAMIC SCHOOL

        መፍቱሀ ዓሊይ መስጂድ የሚገኘዉ የሴቶች ጀመአዉ ላይ አሚር ስለሆነች እኔ በተለለያዩ ነገር እንድሳተፍ አደረገችኝ፡፡በሳምንት ቅዳሜ የኛ የሴቶች ጀመአ ዝግጅት አለን.... እናም እሳተፋለሁ.., ሁሌም መፍቱሀ አንቺ ተሰጥኦ ታለንት አለሽ ትለኛለች፡፡ መፍቱሀ ግጥም ትፅፍ እና እኔ ነኝ የማቀርበዉ....መነባነብ ለራሱ እንደ እኔ የሚሆን የለም .....እናም በመሀል ቀልድም ሲያስፈልግ እኔ ነበርኩ ፈታ የማረጋቸዉ፡፡
በሂደት እኔዉ የተለያዩ ግጥሞች ታሪኮች ፅፌ ለሷ አነብላታለሁ እሷም ይሄ ጀመአ ላይ መቅረብ አለበት እያለች የተለያዩ ኢስላማዊ ይዘት ያላቸዉ ዝግጅቶች አቅራቢ ሆንኩኝ፡፡

ድፍረቴን ተስጦኦየን አይተዉ ዝግጅት ሲኖር የጀመአዉ መድረክ መሪ አስተዋዋቂ እኔዉ ሆንኩኝ፡፡ ፕሮግራም መሪ..ፕሮግራም ያላቸዉ...እናም የሚቀርቡትን ነገሮች ይመጥናል አይመጥንም እያልኩ እኔዉ እገመግማለሁ፡፡
ዝግጅት ሲኖር ሀሳባቸዉን ሁሉም ለኔ ትተዋል፡፡ እኔም በዚህ መድረክ መምራት ማንንም አልፈራም

መፍቱሀን ዛሬም ነገም ለወደፊትም ብሆን ዉለታዉን መመለስ ባልችልም ሁሌም ሳመሰግናት እና በልቤ ዉስጥ አስቀምጫታለሁ
★★★ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል በጎ ነገር ላደረገላችሁ ሰዉ ወረታዉን መልሱ ..ካልቻላችሁ ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን በማለት ዱዐ አርጉለት ብለዋል ፡፡
በሌላ ሀዲሳቸዉ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ሰዉ ላደረገለት በጎ ተግባር ሰዉን ያላመሰገነ አላህንም አያመሰግንም ..ብለዋል፡፡ ሁሌም ቢሆንም ለእኔም ዱአ ሳደርግ ለመፍቱሀም አብሬ ዱአ አደርጋለሁ

ይሄ ጀመአ የሴት ብቻ አይደለም ወንዶችም እራሳቸዉን ችለዉ አላቸዉ የጀመአችን ስም አንድ ነዉ Telegram ..Whatsap..Youtube አድራሻዎች አሉን በጂማ ታዋቂ ነዉ፡፡ ፋዉንዴሽንም አለዉ የቲሞችን የተቸገሩን ጧሪ ቀባሪ የሌሊቸዉን ወረሀዊ መዋጮ አለ በተጨማሪም ከባለሀብቶች በማስተባበር እየሰበሰብን በወር ብዙ ችግረኞችን የቲሞችን እንደጉማለን

   ጅልባብ ለባሽ ከሆንኩ ቡሀላ ከጀመአም ልጆች መስጊድ ከሌላም ቦታ የምንገናኝ ሙስሊም እህቶቼ በጣም ይቀርቡኛል ፡፡ አንድ አባባል አለ አንተ ጥሩ ቦታ ከሆንክ የሚቀርቡህ ጥሩ ነገር ነዉ፡፡ መጥፎ ቦታ ከሆንክ የሚጠጋህ መጥፎ ባለጌ ሰዉ ነዉ...አላህ ከወደደህ ሁሉ ሰዉ ይወደሀል አይደል የተባለዉ ሀቅ ነዉ ፡፡ እኔ ለዲኔ ጠንካራ ሆንኩኝ ለሊት እየተነሳሁ መስገድ ሱና ሶላቶች እና ሱና ፆሞችን መፆም ከጀመርኩ ቆየሁ ፡፡

ግን ሁሌ በመደጋገም ዱአ ማደርገዉ አለ ...አላህ ሆይ ከማንነቴ የሚወደኝ እኔን የሚረዳኝ የትዳር አጋር ስጠኝ እያልኩ ዱአ አደርጋለሁ

በጀመአ ዝግጅት መድረክ መሪ በሆንከበት ጊዜ ብዙ ሰዉ አይን ዉስጥ መግባት እና ለኔ ጥሩ ጥሩ ሲለሚወራ ለሰሚ ጆሮ አገኘሁ፡፡ እኔ ዝግጅት መሪ ስሆን አዳራሽ ተከራይተን ዝግጅት ስናዘጋጅ ወንዶች በመጋረጃ ተከልለዉ ይታደማሉ ፡፡ እኔ መድረክ መሪ በመሆኔ ከተለያዩ ወንዶች አድናቆት እየጎረፈ ነዉ..........፡


#ክፍል

ይ.........ቀ.............
.......ጥ...........ላ.................ል

JOIN
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•