Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ አራት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ማንንም እንዳፈሪ ጅልባቡን ሳታወልቂ ለብሰሽዉ ነይ አለችኝ........
የመፍቱሀ ንግግር ልቤ ዉስጥ ገባ ..ሰዉ ምን ይለኛል የሚል ፍርሀትን አስወግጄ ወኔ ፈጠረብኝ ....ማንንም አልፈራም ደግሞ ለዘንድሮ ሰዉ ብየ ጅልባቡን እንደለበስኩኝ ከቤቴ ወደ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ መሔድ ጀመርኩኝ....ግን እደሄድኩ የመጀመሪያየ ስለሆነ እየተንቀጠቀጥኩ እየፈራሁኝ ነዉ፡፡ ሰዉ ሁሉ በመንገድ ስሄድ ሲያየኝ ምን ሁና ነዉ የሚለኝ ይመስለኛል.... በጣም ነበር የማያስፈራዉ፡፡ እንደ ምንም ብየ ኮሌጅ ደረስኩኝ...

ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ሁሉም እየተጠቋቆሙ እኔን ነዉ የሚያዩት ...በጣም ነዉ የገረማቸዉ ያልጠበቁት ተአምር ነዉ የሆነባቸዉ፡፡ ከትምህርት ቤታችን ቁጥር አንድ በፋሽን ልብስ ዘናጭ የተባልኩኝ ተማሪ ዛሬ ጅልባብ ለብሼ ከች ስል ሁሉም ገርሞት መልኬ እስከሚገፍ ተመለከቱኝ ግን እኔን ደፍሮ ለመናገር የሞከረ የለም ዝም አሉኝ

  መፍቱሀ ከሩቁ አየችኝ ፊቷ በደስታ የሚያበራ ይመስላል ..ከተቀመጠችበት ቁማ ጠበቀችኝ እሷ ጋር ስደርስ ነዋልየ ወላሂ ለአላህ ብየ እወድሻለሁ ዛሬ ደግሞ በጣም አስደሰትሽኝ ብላ በደስታ እቅፍ አድርጋ ሳመችኝ....ደስታዋን የምገልፅበት ቃላት አጠራት የደስታ እምባ እያነባች በለበሰችዉ ክሪም እምባዋን ትጠርግና አይን አይኔን ታየኛለች መልሳ እቅፏ ዉስጥ ታስገባኝ እና ትስመኛለች፡፡ ነዋልየ አኮራሽኝ ወላሂ እንዴት እንዳስደሰትሽኝ ...አላህ ሁሌም ያስደስትሽ ነዋልየ ወላሂ እንዴት እንዳማረብሽ ልነግርሽ አልችልም፡፡ ደስታየን አንድ ቀን ብቻ እንዳታደርጊዉ ነገም ለብሰሽ እንድመጪ አንድ ቀን ብቻ ለብሰሽ እንዳታወልቂዉ አለችኝ
......እኔም እሺ መፍቱሀ ኢንሻ አላህ አለብሳለሁ አልኳት፡፡ ክላስ ገብተን ተምረን ወደ ቤታችን ተለያየን፡፡

እድሜ ለሰጠዉ ሰዉ ወደ ሞት እየተጓዝን ቢሆንም ከቀናችን አንድ ቀን ለመቀነስ መንጋቱ አይቀርም..ይሄዉ ዛሬም ነጋ ..እንደትናቱ ጅልባቤን ለብሼ ወደ ኮሌጅ አመራሁኝ ...እዛም እንደ ደረስኩ የትምህርት ቤት ልጆች እንደትናትናዉ ለመናገር አልፈሩም ..የብዙ ሰዉ አስተያየት ተቀበልኩ፡፡ የሚገርማችሁ ክርስቲያን የሆኑ የኛ ክላስ ልጆችና ትምህርት ቤት የምግባባቸዉም የማልግባባቸዉም ነዋል ይሄ አለባብስ አምሮብሻል አታዉልቂዉ .....ትናንት ለብሰሽዉ ስናይሽ ለአንድ ቀን ብቻ የለበሽዉ መስሎን ነበር የሁሌም ልብስሽ ብታደርጊዉ ያምርብሻል አሉኝ፡፡
ብዝዎቹ ክርስቲያን የክላስ ልጆችም ነዋል አንቺ ቀይ ስለሆንሽ በጥቁር ጅልባብ ከሁሉም ሴቶች አንቺ ላይ አምሮብሻል አሉኝ ፡

አስተያየት ከሰጡኝ ሁሉም ክርስቲያኖች 100% እንደአማረብኝ አታዉልቂዉ አምሮብሻል ብለዉ መሰከሩልኝ ፡፡ እዉነታቸዉን ነዉ አልተሳሳቱም መልኬ በጣም ቀይ ነኝ ጥቁር ጅልባቡ ሲጨመርበት ምንም የማይሳነዉ ጀሊሉ አምጥቶ ዉበቱን ደፋብኝ....

ብሩክታይትም ደስ ብሏት ማርያምን አምሮብሻል እንዳታወልቂ አለችኝ፡፡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶቼም ማሻ አላህ አሉኝ በጣም ደስታ ተሰማኝ፡፡

ደግሞ በተዘዋዋሪ ሙስሊም ሁነዉ ፋሽን ተከታይ ሴቶች  ደግሞ ምን ሁነሽ ጅልባብ ለበሽ?? አንቺ ገና ነሽ ወጣት ነሽ እንደ በፊቱ ብዘንጪ ነዉ የሚያምርብሽ እያሉ በለበስኩት ጅልባብ አንቋሸሹብኝ ወላሂል አዚም በጣም ተአጀብኩኝ ሙስሊሞቹ ከሰጡኝ አስተያየት 35% መልበሴን የተቃወሙ ናቸዉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚያመለክተዉ ዲነል ኢስላም ላይ ገና አለመሰራቱ እና ሙስሊም ናቸዉ እንጂ ኢስላም ሀይማኖት ምን እንደሆነ ገና የሚቀረን ማህበረሰቦች ነን ያለነዉ ማለት ነዉ...አሁን ላይ በእንደዚህ ያሉ የሀይማኖት ተከታዮች ተተብትቦ ዲነል ኢስላም የምናሰድበዉ ፡፡ ዲነል ኢስላም መመዘን ያለበት በሀይማኖቱ ዉብነት ለሰዉ ልጅ ፍትህ እንደሆነ እንጂ በዲነል ኢስላም አንዳንድ ተከታዮቹ ኢስላም ቢፈተሽ አንድም ሰዉ ወደ ኢስላም ባልገባ ነበር..ግን ምን ይደረጋል ዲነል ኢስላም በአንተም በአንቺም በእሱም በእሷም በእነሱም በእነዛም የሚመዘን አይደለም ሀቅ በያዙ ደጋግ አቢድ ሷሊህ በሆኑ ባርያዎቹ እንጂ፡፡

ክርሰቲያኖች በመንገድ የሚያገኙኝ አድንቀዉኝ ሙስሊሞቹ እንደዚህ ሲያንቋሽሹኝ በእኔ ሳይሆን ሙስሊም ሁነዉ እንደዚህ በማሰባቸዉ አፈርኩባቸዉ፡፡
      የቱርክ የቻይና የዱባይ ፋሽን ተብየ ልብስ መልበስ ትቼ ጅልባብ ብቻ መልበስ
ጀመርኩኝ....,ልብስም ከገዛሁ የምገዛዉ የተለያዩ ጅልባቦች በተለያዩ ከለሮች እና የጅልባብ ማላበሻ ክሪም ብቻ ሆነ፡፡

አንድ ቀን እኔና ብሩክቲ አንድ ላይ ቁመን
አንድ ወንድ ክርስቲያን የክፍላችን ልጅ እኔ እና ብሩክቲን መጥቶ ሰላም አለን.... ወንድ ልጅ ጋር መጨባበጥ ሀራም እንደሆነ አቃለሁኝ ግን እሱን እንዳይደብረዉ ብየ ነበር ሰላም ያልኩት
...... ብሩክቲም እንዴት ወንድ ሰላም ትያለሽ ?? መፍቱሀ የአጂ ነብይን እጅ የጨበጠ ጀሀነም እሳትን እንደጨበጠ ነዉ ስትል ሰምቻታለሁ እንዴት ትጨብጫለሽ ? ደግም ከአሁን ቡሀላ ጅልባብ ለብሰሻል ወንድ ልጅ መጨበጥም አቁሚ አለችኝ ክርስቲያን ጓደኛየ ብሩክቲ
....እኔም እሺ ልክ ነሽ ብሩክቲ አልኳት ፡፡ በጣም አፈርኩኝ ብሩክቲ ክርስቲያን ሁና ስለ ኢስላም አዉቃ እኔ እንዴት እያወኩኝ መተግበር አቃተኝ ?? እንዴት አጂ ነብይ መጨበጥ ሀራም መሆኑን እያወኩ እንዴት ሰላም እላለሁ ?? ከአሁን ቡሀላ ወንድን ልጅ ማንም ይሁን ማንም ሰላም ላልል ለራሴ ቃል ገባሁ

   መፍቱሀ ከትምህርት ሰአት ዉጭ መርከዝ ገብተሽ ተማሪ አለችኝ...
... እኔም መርሀባ በማለት ጅሬን ሰፈር የሚገኘዉ አባጅፋር መርከዝ ተመዘገብኩኝ ቁርአኔን ሙራጅአ ማድረግ ጀመሬ ብዙም ሳልቆይ ጨረስኩኝ ኪታብ መቅራትም ጀመርኩኝ በኡስሉሰላሳ ጀመርኩኝ በሉገል መራም ሌላ ኪታቦች እዛዉ ቀራሁኝ ....ሰአት እያመቻቸሁ ሌላ ቦታ ሪያደሷሊህን መቅራት ጀመርኩኝ.....እኛ ሰፈር ያለዉ አጂፕ መስጊድ ሰአት እያመቻቸሁ ቁርአን ተፍሲር መቅራት ተያይዠዋለሁ፡፡
የመፍቱሀ ግፊት ለኔ በሒወቴ መስመር የያዝኩበት ኪታብ የቀራሁበት ዲነል ኢስላምን ያወኩበት ነዉ ...መፍቱሀ ለኔ ሁለ ነገሬ ናት
#የትአሉ_ለአላህ_ብለዉ_የተዋደዱ!!!!!"
መፍቱሀን አላህ የሰጠኝ ለሂድያ ስበብ የሆነችኝ የጨለመዉን ሒወቴን መብራት ያበራችልኝ ናት

★★★★ባልደረባክን ጓደኛክን ምረጥ ……
ተወዳጁ ነብያችን ﷺ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ:-
ሰውየው ሀይማኖት በጓደኛው ላይ ነው አንድኛችሁ ባልደረባ አድርጎ ወደያዘው ሰውዬ ይመልከት

>>>አሏህ ይዘንላቸውና ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ:- የኸይር ባልተቤቶች የሆኑትን ሰዎች ጓደኛ አድርገክ በመያዝ ጓጓ ትኩረት አድርግ መልካም ጓደኞች በጠመምክ ጊዜ ይመሩካል፣ በተሳሳትክ ጊዜ ያቀኑካል፣ አሏህን በረሳክ ጊዜ ያስታውሱካል፣ ጃሂል ( መሀይም) በሆንክ ጊዜ ያስተምሩካል።ብለዋል