Get Mystery Box with random crypto!

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ መመሪያዎችን አጸደቀ፡፡ ለሴኔቱ | Injibara University

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ መመሪያዎችን አጸደቀ፡፡

ለሴኔቱ የቀረቡት አጀንዳዎች፡-
 የአካዳሚክ ካሌንደር ማጽደቅ፣
 በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎችን ውጤት ማጽደቅ፣
 የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ሥርዓተ ትምህርት (Curriculum)ማጽደቅ፣
 የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ህግ ማጽደቅ፣
 የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም እና የአገው ጥናት ኢንስትቲዩት የሥራ መመሪያን (Guide line) ን ማጽደቅ ሲሆኑ በእያንዳንዳቸው ጉዳዮች ላይ ሴኔቱ በጥልቅ በመወያየት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህም መሰረት የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከትምህርቱ ተፈጥሯዊ ጠባይ አንጻር የትምህርት አሠጣጥ ፕሮግራሙ ከሌሎች የተለየ በመሆኑ የቀረበው የጊዜ ሰሌዳ ተገምግሞ ጸድቋል።

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0DUe9P9rWJ4xf3qBXzwXgRg7uM1e698jPnqm44JkgJNDa6s158nBo69yuZ1UFcbkVl/?app=fbl