Get Mystery Box with random crypto!

'አገው ድጋግ' (የአገው ዣንጥላ) አሠራር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ማኅ | Injibara University

"አገው ድጋግ" (የአገው ዣንጥላ) አሠራር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አገልግሎት እና የአገው ጥናት ኢንስቲትዩት ከአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እንዲሁም ከእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር "አገው ድጋግ" (የአገው ዣንጥላ)አሰራር ለተከታታይ ሰባት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ።

በስልጠናው የማስጀመሪያ መረሃ ግብር የተገኙት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ም/ማ/አገ/ም/ፕሬዚዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ስልጠናው የሀገር በቀል እውቀትን በመጠበቅ እንዲሁም በቀጣይነት ባህልን እና እሴትን አስጠብቆ የማቆየት ዓላማ እንዳለው ገልጸዋል። የሙያ እና ቴክኒክ ኮሌጆችም በእደ ጥበብ የተለዩትን የሀገር በቀል እውቀቶችን ከማልማትና ከማስጠበቅ አንጻር እንደ አንድ የትምህርት አይነት አድርጎ ለተማሪዎች በማስተማር ወደ ትውልድ የማስተላለፍና ጠብቆ የማቆየት ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ለይኩን ሲሳይ በበኩላቸው "አገው ድጋግ" /የአገው ዣንጥላ/ከድሮ ጊዜ ጀምሮ በአዊ ማህበረሰብ ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው መሆኑን ጠቅሰው ዘመናዊ ጥላ እስኪመጣ ድረስ ሴቶች እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ወንዶች በዚህ ጥላ ከፀሐይና ከዝናብ ይጠለሉ እንደነበር እና ሠርግም የሚከናወነው በዚህ ጥላ እንደነበር ታሪኩን አስታውሰዋል።
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02ZotesaDsEjJcTCAtX6MAerwrKf9C4gf4wXLMBqfLyKVHKuJtxPgBB5GTZaDCC6Z9l/?app=fbl