Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ፡- በ2015 ዓ.ም የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ | Injibara University

ማስታወቂያ፡-
በ2015 ዓ.ም የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦
የማካካሻ ትምህርት(Remedial) ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ እንዲሁም መጋቢት 6/2015 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ
 የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፤
 ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፤
 3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ እና
 አጋዥ የትምህርት መጽሓፍትን ይዘው መምጣት የሚችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የካቲት 24/2015 ዓ.ም ፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ለተጨማሪ መረጃ/ for more Information
ለቴሌግራም-https://t.me/injiuniversity
ለኢንስታግራም -https://www.instagram.com/injibara12
ለዌብ ሳይት- https://www.inu.edu.et/
ለፌስ ቡክ ገፃችን- https://www.facebook. Com/injibaruni
ለኢሜይል- injibarau@gmail.com
ለInstitution Email -injibarauniversity@inu.edu.et
ለትዊተር- Twitter (https://twitter.com/injibara_Inu/)
በተጨማሪም የዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉን!
https://www.youtube.com/c/injibarauniversity
Explore Your Creative Potential!