Get Mystery Box with random crypto!

የዓድዋ ድል በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡ “አንድነት፣ጀግነትእና ፅናት” በሚል | Injibara University

የዓድዋ ድል በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡

“አንድነት፣ጀግነትእና ፅናት” በሚል መሪ ቃል 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን እና ተማሪዎች የሃይማኖት አባቶች የአገው ፈረሰኞች አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የካቲት 23/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

የህዝብ እና ውጭ ግንኙነት ከታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር በጋራ ባዘጋጀው የዓደዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ”የዓድዋ ድል እና የሴቶች ሚና ” የሚል መነሻ ጽሑፍም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በበዓሉ ዝግጅት የተገኙት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ድል መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጫፍ እስከ ጫፍ በአንድ ዓላማ በመሳተፍ ጠላትን ድል አድርገው ያስረከቡን ታሪክ በመሆኑ ሁላችንም አንድነትን፣ ጀግነንት እና ጽናትን ይዘን በጋራ መስራት እና ታሪካችንን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02edtfbDcb2czue1zosTpnPAKappKCchCkQjejk7QRGxqwk9KHvGxAhddUkaa5J5d7l/?app=fbl