Get Mystery Box with random crypto!

በ2015 ዓ.ም ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ | Injibara University

በ2015 ዓ.ም ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ጽዱ፣ ውብ፣ በትምህርት ጥራት ተመራጭ፣ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የመጀመሪያ ምርጫችሁ አድርጋችሁ እንድትመርጡ በአክብሮት እንጋብዛለን!

ስለ እንጅባራ በጥቂቱ፡-
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ መርኃ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 450 ኪ.ሜ ከአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ደግሞ 112 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አካባቢው ነፋሻማና ለጤና ምቹ በመሆኑ ብዙዎቹ ለኑሮ የሚመርጡትም ነው እንጅባራ፡፡
ከግንባታ ሥራዎች ጎን ለጎን አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን የጀመረው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ምቹ፣ ጽዱና ለዐይን ማራኪ ገጽታን ተላብሷል፡፡ በዚህም ከተማሪዎች እና ከተለያዩ አካላት ምስጋና እና እውቅና አግኝቷል፡፡
በ2014 ዓ.ም በተደረገው የተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ምርጫም በሀገሪቱ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከምርጥ አሥር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኗል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0L36k3hMbbonN2cbnDfYWPamwBvEaoxta965td9Wr68ig7ef9vA6sPXUpAFoJThzql/?app=fbl