Get Mystery Box with random crypto!

'አምራች ዘማች' በሚል መሪ ቃል የተከበረው 83ኛው የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ | Injibara University

"አምራች ዘማች" በሚል መሪ ቃል የተከበረው 83ኛው የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ይህን ድንቅ በዓል በኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲመዘገብ ክፍተኛ እገዛ ማድረጉ በማድረጉም ምስጋና ተችሮታል፡፡
በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ አቶ እንግዳ ዳኛው እንደተናገሩት የአገው ህዝብ ህግ አክባሪ፣ በኢትጵያ ታሪክ የራሱን አሻራ ያሳረፈ እና የራሱን ባህል እና እሴት ጠብቆ የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዋና አስተዳደሪው ዩኒቨርሲቲው ላደረገው ሁሉን አቀፍ አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡
በበዓሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ( ዶ/ር) የአገው ፈረሰኞች ማህበር 83 ዓመታትን መሻገሩ የፅናት ተምሳሌት መሆኑን በመጥቀስ በዓሉ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ መስራት እንደሚገባ ተናግረው በዓሉ የተሳካ እንዲሆን በሁሉም ዘርፍ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በበዓሉ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየ፣ የአማራ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ፣ አርቲስት ይሁኔ በላይን ን ጨምሮ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ጥር 23/2015 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩነቨርሲቲ