Get Mystery Box with random crypto!

በስጋዲ ሞዴል ችግኝ ጣቢያ የሥራ ጉብኝት ተካሄደ፡፡ ---------------- የእንጅባራ ዩኒቨር | Injibara University

በስጋዲ ሞዴል ችግኝ ጣቢያ የሥራ ጉብኝት ተካሄደ፡፡
----------------

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና፣ ምግብ እና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ እየተሰራ በሚገኘው ጓንጓ ወረዳ ስጋዲ ሞዴል ችግኝ ጣቢያ ላይ የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት ተካሂዷል።

በጉብኝቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመባቸው ሶስት ዋና ዋና ተልዕኮዎች አንዱ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ተልዕኮ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር በአረንጓዴ ልማት ላይ በሰፊው እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ከዚህ አንጻር በስጋዲ ሞዴል የችግኝ ጣቢያ ላይ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ችግኝ የማፍላት ሂደት መጀመሩን የገለጹት ም/ፕሬዝደንቱ ቦታውን ለረዥም ጊዜ የሚጠቅም የአንድ ትልቅ የችግኝ ጣቢያ በማድረግ የምርምር እና የመማር ማስተማር ሥራዎች በተግባር የሚከወኑበት እንዲሁም ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞችን አዘጋጅቶ ተደራሽ ለማድረግ በዘርፉ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን በመመደብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚህየችግኝ ጣቢያ ላይ ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ያቀረበውን የቦታ ጥያቄ ሳያቅማሙ ተቀብለው ላስተናገዱ የጓንጓ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
...

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0GEhfN8PaeKpo4MGEspYxeQcMTnj1nVMwxJXVfqZtya7Fx9SS2V56zSgFsaGNCgbNl/?app=fbl
ጥር 5/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ