Get Mystery Box with random crypto!

የገና 2015 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከበረ። የ | Injibara University

የገና 2015 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከበረ።

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው መመገቢያ አዳራሽ ከተማሪዎች ጋር በዓሉ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ተማሪዎች ከቤተሰብ ተለይተው እንደዚህ ዓይነት በዓላትን ሲያሳልፉ ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ዩኒቨርሲቲው ለበዓል የሚሆን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዳደረገ ገልፀው በዓሉ የሰላምና የፍቅር የአንድነት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የገና በዓል አስመልክቶ ቀደም ብሎ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን በማድረግ በዓሉን ለማክበር በመመገቢያ አዳራሹ ውስጥ ልዩ ልዩ የበዓሉን ድባብ ለተማሪዎች የሚያስተጋቡ መስተንግዶዎች ቀርበው በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የግቢው የፀጥታና ደህንነት አባላትና በግቢው ውስጥ በፀጥታና ደህንነት ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላትም በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

ታኅሳስ 29/2015፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ