Get Mystery Box with random crypto!

መሰረታዊ የአመራርነት ጥበብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡ /////////////// ለእንጅባራ ዩ | Injibara University

መሰረታዊ የአመራርነት ጥበብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡
///////////////
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መካከለኛና መሠረታዊ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና በዋናነት ስራ አመራር ላይ ያተኮረና የመካከለኛ አመራሩን የመምራት አቅም ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የሥልጠናውን መርሐ ግብር በይፋ ሲያስጀምሩ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የተሻለ ግንዛቤና ልምድ እንዲወስዱ በማሰብ የካበተ ልምድ ያላቸውን አሠልጣኞች በመጋበዝ ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቅሰው ከስልጠናው በኋላ የአመራርነት ክህሎቱን በማሻሻል የሚሠራበትን ኃላፊነት ውጤታማ የሚያደርግ ግብዓት እንደሚገኝ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ሰው ኃብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ጥላሁን ስልጠናው መከካለኛ እና መሠረታዊ አመራሮች የመምራት አቅማቸውን ለማሳደግ እና ለማሻሻል ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰው ለ120 የዩኒቨርሲቲው አመራሮች መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ፣ የውሳኔ አሳጣጥና የችግር አፈታት፣ የአስተሳሰብ ውቅር፣ የተቋማዊ ስነ ምግባር ሥራ አመራር፣ የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ፣ የለውጥ አመራር፣ የሥራ አመራር ተግባቦት፣ ሁለንተናዊ ለውጥ እና የቡድን ሥራ የሚሉ ጉዳዮች በስልጠናው ተዳሰዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በሥራ አመራር ሥልጠና የካበተ ልምድ ያላቸው ዶ/ር ተመስገን ዳኘ እና ኢትዮጵያ ሲቪል ስርቪስ እና የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩት የማኔጅመንት አማካሪ ዶ/ር ዮሴፍ ውባለም ናቸው።

ስልጠናው ለተከታታይ ሦስት ቀን የተሰጠ ሲሆን በዛሬው እለት ተጠናቋል።

ህዳር 25/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ