Get Mystery Box with random crypto!

በግብርና፣ ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር ሥራዎች አፈጻጸም እና የወደፊት አቅጣጫ ላ | Injibara University

በግብርና፣ ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር ሥራዎች አፈጻጸም እና የወደፊት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ በኮሌጁ የተከናወኑ የግብርና ምርምር ሥራዎች አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በከፍተኛ አመራሩ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ተነስተው የወደፊት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
የኮሌጁ ዲን ሀብታሙ አድማስ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በግብርናው ዘርፍ በተካሄዱ ምርመሮች ላይ ያለውን አፈፃፀም በመገምገም ግብዓት የሚገኝበት መድረክ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ግብርና የማህበረሰቡ ህልውና እንዲሁም የሀገር ኢኮኖሚ ዋልታ መሆኑን የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከለያቸው የትኩረት መስኮች በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል።
"የምርምር አብዮት" ያስፈልገናል ያሉት ፕሬዝደንቱ ከዚህ በፊት በተካሄዱ የምርምር ሥራዎች ላይ የነበሩትን ክፍተቶች በማሻሻል ለወደፊቱ በማህበረሰቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ችግር ፈቺና በሁሉም የግብርና ዘርፎች ውጤታማ የሚያደርጉ ጥናትና ምርምሮችን ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) በበኩላቸው የምርምር ሃሳቦችን ተገቢነት ከመቅረፅ ጀምሮ ሁሉም ተመራማሪ ሃላፊነት እንዳለበት ተናግረው ተናገረው በቅርቡ ወደ ዩኒቨርሲቲው የተቀላቀሉ የካበተ ልምድ ያላቸው መምህራንም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ እምነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የኮሌጁ የምርምር ሥራዎች ግምገማ ሪፖርት በአቶ ዮናስ ደረበ እና የመስክ ጉብኝት ግምገማ ብርሃኔ (ዶ/ር) አማካኝነት የቀረበ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን በተነሱ አስተያየቶች ዳብሮ በከፍተኛ አመራሩ የወደፊት አቅጣጫም ተቀምጧል።
ኅዳር 16/2015 ዓ.ም