Get Mystery Box with random crypto!

በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ ጉብኝት ተካሄደ፡፡ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና፣ ምግብና አየር ን | Injibara University

በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና፣ ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ ከፋሲሊቲ ማኔጅመንት ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተዘጋጀው ችግኝ ጣቢያ የተለያየ ዝርያ ያለቸውን ችግኞች በማፍላት ለተለያዩ ተቋማት፣ ለተራቆቱ ቦታዎች ለውበትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚሆኑ ችግኞች ተሰራጭተው መተከላቸው ይታወሳል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የግብርና፣ ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ ሀብታሙ አድማስ (ዶ/ር) ከኮሌጁ መምህራን ጋር በመሆን በየወረዳዎቹ በማህበረሰብ አገልግሎት በኩል ተሰራጭተው የተተከሉ ችግኞች ያሉበትን ሁኔታ በመጎብኘትና በመገምገም ከቀበሌ ሥራ አስኪያጆችና የተቋም መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የተተከሉት ችግኞች በጥሩ እንክብካቤና አያያዝ ላይ ያሉ መሆናቸውን በመጎብኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ በትብብር ከሚሰሩ አካላት ጋር እነዚህን መሰል ተግባራት በቀጣይነት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአረንጓዴ ልማት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፈቃዱ ጥሩነህ በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ ያለውን የደን ሽፋን ከፍ ለማድረግ በዩኒቨርሲቲው የችግኝ ጣቢያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሚተከሉ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ገልፀው በችግኝ ጣቢያው ውስጥ ከሚሰሩት በርካታ ሥራዎች በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት ተሰራጭተው የተተከሉ ችግኞችን በቅርብ ርቀት በየጊዜው የክትትልና ቁጥጥር ተግባራትን እንደሚያከናወን ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ መርሐ ግብሩ ዳንግላ ከተማ 02 ቀበሌ ለመንገድ ዳር ውበት የተተከሉ ችግኞች፣ አዲስ ቅዳም ከተማ የአረንጓዴ ልማት ክልል ውስጥ የተተከሉ ችግኞች፣ እንጅባራ አጠ/1ኛ ደ/ት/ቤትን ለማስዋብ የተተከሉ ችግኞችና በባንጃ ወረዳ የገጠር ቀበሌ የተተከሉ ችግኞች ተካተዋል፡፡
ኅዳር 13/2015 ዓ.ም