Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡ ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀን በዓለም አ | Injibara University

ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡

ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ፤ በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ህፃናት ማቆያ ማዕከል ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ለቤተሰቦቻቸው በማሰብ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ጤንነታቸው ተጠብቆ፣ እድገታቸው ዳብሮ አዕምሯቸው ጎልብቶ በሰላም እንዲያድጉ፤ ወላጆችም ያለምንም ችግር በተሳካ ሁኔታ ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት ደረጃውን የጠበቀ የኅጻናት ማቆያ ማዕከል መክፈቱን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ማዕከሉ መከፈቱ ብቻ ግብ አለመሆኑንና ህፃናት የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲያገኙ የማዕከሉ ሠራተኞች፣ ወላጆችና ዩኒቨርሲቲው የሚጠበቅቸውን ኃላፊነት መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የማዕከሉ ሠራተኞችም ለህፃናት የሚገባውን እንክብካቤ መስጠት እንዳለባቸው በማሳሰብ የዩኒቨርሲቲው አመራር ለህጻናት ማቆያ ማዕከሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ግብዓት እንደሚያሟላ ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴቶች፣ ኅፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ደብሪቱ ምናየሁ በበኩላቸው የዩቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ኃላፊነት ወስዶ በቁርጠንኝነት ይህን ማእከል በመገንባቱ ምስጋናቸውን አቅርበው ዓለም አቀፍ የኅፃናት ቀን ሲከበር ለህፃናት የሚያስፈልገውን እንክብካቤ በማድረግ ኃላፊነት ሁሉም ሊወስድ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ኅዳር 13/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ