Get Mystery Box with random crypto!

እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ለሁለት ትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ -------------- | Injibara University

እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ለሁለት ትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
--------------
ዩኒቨርሲቲው በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሁለት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቢሮ ቁሳቁስ እና ሲሚንቶ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን ዶ/ር እንደተናገሩት የትምህርትን ጥራትን ለማስጠበቅ ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ገልፀው በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለአንከሽ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለአንድነት አጠቃላይ 1ኛ ትምህርት ቤት ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም አንክሽ ትምህርት ቤት አዲስ እና ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚመጡ ብዛት ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበት በመሆኑ በተጨማሪም አንድነት አጠቃላይ ትምህር ቤትም በማህበረሰቡ የሚሠራ ከመሆኑ አንፃር ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ ለአንክሽ ትምህርት ቤት ግምቱ ከ105 ሽህ ብር በላይ ግምት የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛ እና ጠመኔ እንዲሁም ለአንድነት አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ ግምቱ 195 ሽህ ብር በላይ የሆነ 100 ኩንታል ሲሚንቶ በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው 300ሺ ብር ግምት ያላቸውን ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ