Get Mystery Box with random crypto!

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የዲጅታል ቤተ-መ | Injibara University

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የዲጅታል ቤተ-መጽሐፍት ማሽን ድጋፍ አደረገ፡፡
-------------
ዩኒቨርሲቲው ለእንጅባራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት እና ለዛጉዌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማሽን ድጋፍ በማድረግ የ S.R.E Digital Liberary ስራ አስጀምሯል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ በእንጅባራ ከተማ ለሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው ከ 500 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የ S.R.E Digital Liberary ሁለት ማሽኖችን ለሁለቱ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ማደረጉን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ማሽኑ ከ60ሺ በላይ ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ያሉ መጽሐፍትን፣ የፕላዝማ የቪዲዮ እና የድምጽ ፋይሎችን፣ የቤተ ሙከራ ምስሎችን ጨምሮ በ21ቋንቋዎች የያዘ በመሆኑ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአዊ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን መኮነን በበኩላቸው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ዘርፍ ቀደም ብሎ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ግምት ያላቸው የቁሳቁስ ግብዓት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው፤ የድጅታል ቤተመጽሐፍት ድጋፉ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ የመምሪያ ኃላፊው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ላደረገላቸው ድጋፍ በዞኑ ማህበረሰብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የእንጅባራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አላዛር አገኘሁ በትምህርት ቤቱ የመጽሐፍት እጥረት የነበረ መሆኑን ጠቅሶ መጻሕፍትን ያለምንም ክፍያ በሶፈት ኮፒ እያወረደ ማንበብ በመቻሉ መደሰቱን ገልጿል፡፡
ሰኔ 24/2014ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ