Get Mystery Box with random crypto!

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የህግ ድጋፍ የመስጫ ማዕከል ከፈተ፡፡ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአካል ጉዳተ | Injibara University

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የህግ ድጋፍ የመስጫ ማዕከል ከፈተ፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ-ደካሞች፣ ለሴቶች፣ ለህፃናት፣ ኤችአይቪ በደማቸው ላለባቸውና ለድሃድሃ የማህበረሰብ ክፍሎች ነፃ የህግ ድጋፍ መስጠት የሚያስችለውን ማዕከል በእንጅባራ ከተማ በይፋ ከፍቷል፡፡

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ የተገኙት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ነፃ የህግ አገልግሎት ቀደም ብሎ መጀመሩን አስታውሰው በአዊ ዞን የህግ የበላይነት እንዲከበርና ፍትህ እንዲሰፍን እና አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችንም በነጻ ህግ የማመከር እና የጥብቅና አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል መከፈቱን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲው ለሚማሩ የህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደ ቤተሙከራ እንደሚያገለግልና ከዚህ በተጨማሪም በዞኑበተለያዩ አካባቢዎች ቅርንጫፍ ማዕከላትን እንደሚከፍት ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የአዊ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉዓለም ደሴ በበኩላቸው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት የመምሪያውን ሥራ እንደሚያግዝ በመጥቀስ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት መምህር ጌትነት አያሌው ደግሞ የህግ ትምህርት ቤቱ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለመሆን ወደ ማዕከላችን የሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳያቸውን በግል ለመከታተልና ጠበቃ ለማቆም የገንዘብ አቅም የሌላቸው መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ከሚኖሩበት ቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በመክፈቻ መርሐ ግብሩ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ም/ፕሬዝዳንቶችና የህግ ትምህርት ቤት መምህራን ተገኝተዋል፡፡

ሰኔ 23/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ