Get Mystery Box with random crypto!

የወለጋ ካርድ ~ የወለጋ ካርድ ያልኩት በአማራ ፖለቲከኞችና አጋፋሪዎቻቸው ክልሉ ውስጥ ሙስሊሞች ላ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የወለጋ ካርድ
~
የወለጋ ካርድ ያልኩት በአማራ ፖለቲከኞችና አጋፋሪዎቻቸው ክልሉ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን የሚያጋልጡ ድምፆችን ለማፈን የሚጠቀሙበትን አፍ ማስያዣ ስልት ነው። እያንዳንዱ ሙስሊሞች ላይ የሚደርስ ጥቃት በተዘገበ ቁጥር "ወለጋ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲፈፀም የት ነበራችሁ?" ይላሉ።
* በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የደረሰ ጥቃት ሲዘገብ "ወለጋ ..." ይላሉ።
* በባህርዳር ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲወራ ይህንኑ የወለጋ ካርድ ይመዛሉ።
* የሞጣ ግድያ ቢዘገብ "ወለጋ ..." ይላሉ።
* የእንፍራንዝ ደረሶች ግድያ ቢዘገብ የተለመደውን የወለጋ ካርድ ይመዛሉ።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች፣ ዝርፊያዎች፣ እገታዎች፣ ማሳደዶች፣ መስጂዶችን ማቃጠል በተዘገቡ ቁጥር ያለ መታከት ይህንኑ ካርድ ይመዛሉ። ሂሳባቸው አጭር ነው። ወለጋ ላይ የደረሰው ጥቃት በቂ ሽፋን ስላልተሰጠው እኛ ስንገድልም፣ ስናፈናቅልም፣ ስናግትም፣ ስንዘርፍም ተቃውሞ ቀርቶ ኮሽታ ሊሰማ አይገባም ነው። እንዲያውም እንደ ተበዳይ ነው የሚተውኑት። "የኛ ማጥቃት ለምንድን ነው የሚራገበው? ደመ መራራ ነን። ነገር ይገንብናል" አይነት ነው ጨዋታው። "አማራ ክልል ኮሽ ሲል ይራገባል" ይላሉ። ያ ሁሉ በጎንደር፣ በደባርቅ፣ በእንፍራንዝ፣ በእስቴ ፣ በቢቸና፣ በሞጣ፣ በባህር ዳር፣ ... የደረሰው መስጂዶችን ማቃጠል፣ የበርካታ ሙስሊም ግድያ፣ እገታ፣ ... ሁሉ ጢኒኒጥ ኮሽታ ብቻ ናት። መስጂድ እንደ ደመራ አንድደው መጨፈራቸው ራሱ እዚህ ግባ የማይባል ተራ ነገር ነው ፣ እንዲሁ ኮሽታ ብቻ። የትኛውም ነገር ይድረስ "አማራ ክልል ውስጥ ኮሽ ሲል... " እያሉ ጥቃቱን ተራ ኮሽታ አድርገው ነው የሚገልፁት። አላህ አናታቸው ኮሽ ያድርገውና።
ከዚያ እኛ ብንበድልም የወለጋው ከኛ ስለሚበልጥ የኛን ብዙም አታስጩሁት ነው የሚሉት። በክልሉ ሙስሊሞች ያነጣጠሩ ጥቃቶች በተዘገቡ ቁጥር ይህንን ካርድ መምዘዝን በቃ ንቃት አድርገውታል። አላማው የተቃውሞ ድምፆችን ማፈን ነው። ሳይወራ፣ ሳይዘገብ መጨረስ። በዚህ አይነት የማንሰማቸው ስንት በደሎች እንደሚኖሩ ማሰብ ይቻላል።
በነዚህ መሰሪዎች ለተሸወዳችሁ ሙስሊሞች ሁሉ! ለመሆኑ በደሉ ምን ሲደርስ ነው "አሁንስ በዛ!" የምትሉት? ነው ወይስ እንዲሁ እያሉ ሁሉንም በየተራ ቢጨርሱም አትነቁም? ለይቶ ማራገብ አለ ካላችሁ የጎደለውን በመሙላት ላይ ስሩ እንጂ በሙስሊም ደም ቁማር ለሚሰራ እባብ ለምን ትወግናላችሁ? የኦሮሚያው ችግር ሽፋን ካላገኘ እናንተ ዘግቡት። "ለምን የኦሮሚያ ሲሆን ...?" የሚላችሁ ሲኖር ነው "ምነው የአማራ ብቻ..." የሚባለው። እንጂ እንዴት በዘር መሰላል ተንጠላጥላችሁ እምነታችሁን ለሚያረክስ፣ ወገኖቻችሁን ለይቶ ለሚያጠቃ አካል ጠበቃ ትሆናላችሁ?! ወላሂ ይሄ የሞኝነት ጥግ ነው።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor