Get Mystery Box with random crypto!

ርችትን የሚመለከት ጥንቃቄ ~ በዒድ ቀን ልጆች ከሚያዘወትሯቸው ጨዋታዎች አንዱ ርችት መተኮስ ነው | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ርችትን የሚመለከት ጥንቃቄ
~
በዒድ ቀን ልጆች ከሚያዘወትሯቸው ጨዋታዎች አንዱ ርችት መተኮስ ነው፡፡ ርችት በተለይም ታላላቆችን ሲያስደነግጥ በብዛት ያጋጥማልና በዒዱ ቀን ሰዎችን ከማስደንገጥ እንዲጠነቀቁ ልጆችን መምከር ጥሩ ነው፡፡ ከዚህም አልፎ አንዳንዴ ለቃጠሎ ሊዳርግ ስለሚችል በተቻለ ከነጭራሹ እንዲርቁት ማድረጉ ይበጃል፡፡ በነገራችን ላይ ርችትን አንዳንድ ዐሊሞች በብዛት ከማይሟላ መስፈርት ጋር ሲፈቅዱት የከለከሉትም ግን አልጠፉም፡፡ ለምሳሌ የሚፈቅዱት ጠቅሰውት ካጋጠመኝ ሰዎችን እንዳያስደነግጥ ከህዝብ ራቅ አድርጎ መጠቀም፣ የወላጆች የቅርብ ክትትል ሊኖር እና መሰል ቅድመ ሁኔታዎች ያስቀምጣሉ፡፡ ሳይከለክሉ እንዲሁ ግን አላስፈላጊ ገንዘብ ማባከን እንደሆነ የጠቀሱም አሉ፡፡ የሚከለክል ፈትዋ ደግሞ ከስር አስፍሬያለሁ፡፡

ጥያቄ፡- “ርችቶችን መሸጥ፣ መግዛትና መጠቀም ብይኑ ምንድን ነው?”

መልስ፡- “ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡ አላህ በነብያችን በሙሐመድ፣ በቤተሰባቸውና ባጠቃላይ በባደረቦቻቸው ላይ ሶላት ያውርድ፡፡ እኔ የሚታየኝ፡- እነሱን መሸጥና መግዛት ሐራም እንደሆነ ነው፡፡ ይህም በሁለት ምክንያት ነው፡-
አንደኛው ምክንያት ገንዘብ ማባከን ነው፡፡ ገንዘብን ማባከን ሐራም ነው፡፡ ነብዩም ﷺ ከዚህ ነገር ከልክለዋል፡፡
ሁለተኛው ምክንያት፡- በነዚህ (ርችቶች) ውስጥ በረባሽ ድምፃቸው ሰዎችን ማስቸገር አለባቸው፡፡ ምናባትም ተቀጣጣይ ነገር ላይ ከወደቁ ገና ያልፈነዱ ስለሆኑ ቃጠሎ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
በነዚህ ሁለት ምክንያቶች ሳቢያ ሐራም እንደሆነና መሸጥም ሆነ መግዛት እንደማይፈቀድ እናምናለን፡፡”

[መጅሙዑል ፈታዋ ሊ ፈዲለቲ ሸይኽ ሙሐመድ ብኒ ሳሊሕ አልዑሠይሚን]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor