Get Mystery Box with random crypto!

ይሄ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተፈፀመ ነው። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ~ 'ምዕራብ ሸዋ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ይሄ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተፈፀመ ነው። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
~
"ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ሸዋ የሚባል አካባቢ አለ። ባሳለፍነው ሳምንት ሰዎች ሱሑር አስረው አረፍ እንዳሉ ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች ተገደሉ። ዛሬም እንደዚሁ ጠዋት 12 ሰዓት እዛው አካባቢ ስልካምባ የሚባል ቦታ 10 የሚደርሱ ሰዎች ተገደሉ። ቤተሰቦቻችን የሚያውቋቸው። የተመታው ተመቶ ሌላው ደግሞ ሸሽቶ ጫካ ተደብቆ ነው ያለው። ብቻ አላህ ይዘንላቸው። አላህ ይማራቸው።

ሶሻል ሚዲያ ለማሰስ ሞክሬ ነበር አንድ እንኳን መረጃውን ያወጣው ሰው የለም።"

ትላንት የተላከልኝ ሜሴጅ ነው። ገና አሁን አየሁት። ሚዲያዎቻችን ስንት ትርኪ ምርኪ ነገሮችን እየዘገቡ እንዲህ አይነት እልቂቶችን ግን ቦታ የሚሰጣቸውም የለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor