Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 88.92K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-25 20:07:50 ማንነት-ፍሮይድ

በተለያዩ ቀናት፣ በተለያዩ ሳምንታት ወይም በተለያዩ አመታት ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች እንዳሉህ ተሰምቶህ አያውቅም? በአንደኛው ቀን ጨዋታ ወዳድ ተጫዋች ትሆንና በሌላኛው ቀን ቁጥጥርን የሚያበዛ ቁጡ ሰው ትሆናለህ፡፡ ሲግመንድ ፍሮይድ ስለ ባህሪ መለዋወጥ የሚለን ነገር አለ፡፡
ከእርሱ በፊት ስለ ሰው ልጆች ስነ-ልቦና ያጠና የለም ባንልም ፍሮይድ ግን በእጅጉ በተለየ ሁኔታ ተመራምሯል እና ዛሬም ድረስ የምንከተላቸውን የሳይኮሎጂ አስተምህሮዎችን ፈልስፏል።
ፍሮይድ የእኛ ማንነት በሶስት ይከፈላል ይለናል፡፡

#ኢጎ; ይህ አሳቢውና ምክንያታዊው ማንነታችን ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የሚያነበውና በአእምሮህ ውስጥ የሚተርክልህም ይህ የማንነት ክፍልህ ነው፡፡ ከሶስቱ ማንነቶችህም በመሃል ላይ ይገኛል።


#ኢድ; ይሄኛው የእንስሳነት ባህሪህን ያጎላዋል፡፡ ወሲባዊ ፍላጎቶችህ፣ በስሜትህ የምትመራባቸው ውሳኔዎችህ እና ሌሎችም ግልፍተኛ ድርጊቶችህ በዚህ የማንነት ክፍልህ ይመራሉ። ልክም እንደ ሰይጣን ሆኖ ውሳኔዎችን እንድትወስን ያጣድፍሃል። የሰደበህን ሰው እንድትደበድብ ወይም ድንጋይ እንድትወረውርበት ያበረታታሃል። ልክ ህጻን ልጅ ሲርበው እንደሚያለቅሰው ይህ ማንነትህ ድርጊቶችህ ስለሚያስከትሉት ውጤት
ሳይጨነቅ ምሱን እንድታመጣለት
ያለቅሳል።

#ሱፐር_ኢጎ; ይህ በአእምሮህ የተቀመጠ ዳኛ ነው፡፡ እንዲህ አታድርግ ነውር ነው፤ ይህን ማድረግህ አንተን እንድትዋረድ ያደርግሃል እያለ ሃሳቦችህ እና ድርጊቶችህ ላይ ሂስ ይሰጣል፡፡ ስለ ማህበረሰቡ ህግ እና ከድርጊትህ በኋላ ስለሚከሰት መጥፎ ነገር አበክሮ ይጨነቃል። ይህ ልክ ነው፤ ይህ ልክ አይደለም እያለ ይመክርሃል።

ለምሳሌ ለፈተና ልታጠና ተቀመጥክ፡፡ ኢድ መጨናነቅ አይወድም፤ እናም በቀስታ ፈታ በል አትጨናነቅ ይልሃል። ወይ ስልክህን አንድታነሳና ፌስቡክ እንድትጠቀም አልያም ከጓደኞችህ ጋር ሄደህ እንድትዝናና ይመክርሃል።

ሱፐር ኢጎ፤ ከኢድ በተቃራኒ፣ ነገሮችን አጋኖ እና መጥፎ አድርጎ ያቀርብልሃል። ዛሬ ካላጠናህ ፈተና ትወድቃለህ፤ ፈተናንም ከወደቅክ ይህን አመት ትደግማለህ... እያለ ያስፈራራሃል።

በመሃል ወይም ምክንያታዊ ማንነትህ ለማስታረቅ ይመጣል፡፡ ራሴን እስክጥል ድረስ መጨናነቅ የለብኝም፤ ሆኖም ግን ለአንድ ሰዓት ያህል አጥንቼ ወደ ጫወታ እሄዳለሁ ይላል፡፡

ፍሮይድ የማንነት ቀውስ የሚመጣው ሶስቱን አጣጥመን ሳንሄድ ስንቀር ነው ይለናል። ሰካራም፣ ሴሰኛ ሰው አይተህ ታውቃለህ ይሄ ሰው የኢድ (የእንስሳነት) ማንነቱ በርትቶበታል፡፡ በተቃራኒው ስለ ሁሉም ነገር የሚጨነቅ እና ፍጹም ለመሆን የሚጥር ሰው ያውቃል? ቋጣሪ፣ ጥንቁቅ አልያም አብዝቶ የሚጨነቅ ይሆናል ... ይህ ሰው የሱፐር ኢጎ (የዳኛው) ማንነት በርትቶበታል፡፡

ሁሌም ቢሆን በሁለቱ ማንነቶቻችን ውስጥ እንዳንዋጥ ራሳችንን ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡ ነገር ሁሉ በጊዜው እና በአግባቡ ሲሆን ያማረ ይሆናል። ጠቢቡ ሰለሞን እንዳለው፡-
“ለማልቀስ ጊዜ አለው፥
ለመሳቅም ጊዜ አለው፤
ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥
ለመዝፈንም ጊዜ አለው።“

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
8.4K viewsedited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 18:46:21 ስነ ስርዓት ሲለው ነብስ ይማር ብሎ መለሰለት
በተስፋሁን ከበደ
ፍራሽ አዳሽ-37

@Human_Intelligence
10.4K viewsedited  15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 12:41:50 ጓደኝነት - አርስቶትል

ለአንደኛው ወዳጅህ ሚስጥርህን ታጋራዋለህ፤ ከሌላኛው ጋር ከቀልድ እና ቧልት ባለፈ አታወራም፤ ይህ ለምን ሆነ?

የሆነ የሕይወት ክፍላችን ላይ የነበረ የልብ ጓደኛችን አሁን ላይ ስለምን ባይተዋር ሆነን?

አርስቶትል ምናልባትም ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይኖረዋል

ታላቅ በሆነ ስራው Nicomachean Ethics ስለ ጓደኝነት የሚለን አለው፡፡ አርስቶትል መልካም ጓደኛ ለመልካም ሕይወት በእጅጉ ያስፈልገናል ይለናል። በመጽሐፉ ላይም ጓደኝነትን በሶስት ይከፍለዋል፡፡

#ጠቃሚ_ጓጸኞች-  ከእነዚህ ጋር ያለህ ወዳጅነት በጥቅም አንጻር የተመሰረተ ነው፡፡ የስራ ባልደረባዎችህ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ዘወትር ቅዳሜ አብረህ ለመጠጣት የምታገኛቸው ወዳጆችህ ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ያገናኛችሁ ነገር ሲወገድ (ስራ ብትቀይር ወይም መጠጣትህን ስታቆም) ጓደኝነታችሁ ያበቃለታል፡፡


#አሰደሳች_ጓደኞች - እነዚህ በአጠገባቸው ስትሆን በፊትህ ፈገግታን ያስቀምጡልሃል፡፡ ቀልደኛ እና ተጫዋች ናቸው። መጮህ፣ መጫወት፣ መቃለድ ይወዳሉ፤ ሆኖም ወዳጅነታቸው አይዘልቅም.... ቀስ በቀስም ካንተ እየራቁ መጥተው ትዝታቸው ብቻ ካንተ ጋር ይቀራል፡፡

#መልካም_ጓደኞች- እነዚህ የአንተን ደስታ አብዝተው የሚሹ፣ በደስታህ የሚደሰቱ፣ በሃዘንህ የሚያዝኑ ናቸው፡፡ ወላጆችህ እንደሆኑ ያህልም ይመክሩሃል.... ይህ ላንተ መልካም ነው፣ ይህ ደግሞ መጥፎ እያሉ መንገድህን ያሳዩሃል። እነዚህ ናቸው ያንተን የልብ ምስጢር የሚያውቁት እነዚህ ናቸው ያንተን እምባም፤ ሳቅም ያዩ፡፡ ሁሌም ቢሆን በዝቅታህም ሆነ በከፍታህ ውስጥ አይለዩህም፡፡

አርስቶትል እንደዚህ አይነት ወዳጆች ይኑርህ ይልሃል፡፡ እነዚህን ነው በሕይወታችን ውስጥ ማቆየት ያለብን።ለእነዚህም ነው ሕይወታችንን አሳልፈን መስጠት የሚገባን፡፡

ምናልባትም ሶስቱንም የሆነ ጓደኛ ሊኖርህ ይችላል አርስቶትልም አስደሳቹን እና ጠቃሚ ጓደኞቻችንን እንድንተው እየመከረንም አይደለም፤ ይልቁኑ ለሁሉም ወዳጆቻችን ጊዜን ልንሰጣቸውና በውስጣቸው ያለውን መልካም ጓደኝነት ልንመለከት ይገባል፡፡

ለመልካም ጓደኞችህም  ታማኝ ሁን መልካም ሕይወት ይሰጡሃልና።

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
13.4K viewsedited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 22:31:11 ራስን ማታለል (Bad Faith)

በሕይወትህ ለምን ያህል ጊዜ ለውድቀትህ ሌሎች ሰዎችን ወይም ሁነቶችን ወቅሰህ ታውቃለህ? እንዲህ ባይሆን ኖሮ እንዲህ እሆን ነበር' ብለህስ ታውቃለህ? አለቃህ፣ መምህራኖችህ፣ ወላጆችህ የሆነ ነገር እንድታደርግ አስገድደውህ ያውቃሉ?

የሃያኛው ክ/ዘመን ፈላስፋ የሆነው ዣን ፖል ሳርት እነዚህን ሃሳቦች በአንድ ሰብስቦ “bad faith' ብሎ ይጠራቸዋል። ይህም ራስን ማታለልን ያመላክታል። ብዙውን ጊዜ በሕይወት ላይ አማራጭ እንደሌለን ለራሳችን እናሳምነዋለን፡፡ ይህን ያደርግነው እንዲህ ስለሆነ ነው የሚል ምክንያትም ከድርጊቶቻችን ጀርባ እናስቀምጣለን። አሁን ላለንበት ደረጃ ያበቁንን አስገዳጅ ምክንያቶች እና ሰበቦች እንደረድራለን፡፡ ራስን ማታለል በዙሪያችን እስር ቤት የመገንባት ያህል ነው።

ማህበረሰቡ ባስቀመጠልን አስገዳጅ ህጎች አልያም ልማዶች ራሳችንን ወስነን በነጻነት ከመምረጥ እንገደባለን፡፡ ለምሳሌ ሜሴጅ እንደላከልሽ ወዲያውኑ አትመልሽለት” አይነት ተራ ሕጎች ጀምሮ እስከ በዳኛ የተደነገጉ ሕጎች ድረስ - የመምረጥ ነጻነታችን ይገደባል።

እናም ራስን ማታለል (bad faith) የሚጀምረው ለውድቀታችን እነዚህን ህጎች ተጠያቂ ስናደርግና በእነርሱ ውስጥ ስንሸሸግ ነው::

እናም ከማህበረሰቡ ተውስን የምንወስዳቸው ብዙ ጭንብሎች አሉን፡፡ በብዙ የሕይወት ክፍሎቻችን ላይ እንዲህ መሆን አለብህ ስለተባልን ልክ እንደ ተዋናይ ሆነን እንተውናለን፡፡
ነገር ግን ይለናል ሳርት፤ ህግ፣ ደንብ፣ ባህል እና ወዘተ... ከመምረጥ አያግዱንም፡፡ ምርጫዎችን የመምረጥ እና የመወሰን ፈቃዱም በእኛ እጅ ላይ ነው ያለው፡፡

በእያንዳንዷ ቅጽበት፣ በእያንዳንዱ ቀን ምርጫዎች አሉን። በእያንዳንዱ ሰከንድም የወደድነውን የመምረጥ ነጻነት አለን። ይህንን ነፃነት ምንም አይነት ነገር ከእኛ ሊቀማን አይችልም፡፡ ነጻ ለመሆንም የተገባን ነን።

በዚሁ ልክም ለእያንዳንዱ ምርጫዎቻችን ውጤት የምንጠየቀው እኛ ብቻ ነን። ቀድሞውኑ በሚገባ አመዛዝነን ካልወሰንን እና መንገዳችን ወደ መጥፎ መዳረሻ ካደረሰን፣ ከእኛ ውጪ ልንከሰው የሚገባ አካል አይኖርም፡፡ ጥፋታችንንም ከማመን ውጪ ማንም ላይ ማላከክ የለብንም፡፡

ነጻ ነህ ... ነጻነትህን ተጠቅመህ መንገድህን ምረጥ...

ምንጭ-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Human_Intelligence
12.8K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 07:33:23 በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ የጥምቀት አደረሳችሁ!

መልካም በዓል !
1.4K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 08:20:10 ከባድ የተባለው ሰንሰለት!

በአለም ላይ ለመበጠስ ከባድ የተባለው ሰንሰለት የብረት ሰንሰለት አይደለም የሰው-ለሰው ሰንሰለት ነው፡፡

1.  የቁሳቁስ ሰንሰለት

ከሰዎች ጋር በቁሳቁስና በገንዘብ ጥገኝነት ከተሳሰራችሁና የእነዚያን ሰዎች ድጎማ ካላገኛችሁና ከእነሱ ውጪ መኖር እንደማትችሉ በማሰብ መንቀሳቀስ ካልቻላችሁ ይህንን ሰንሰለት የቁሳቀሱ ሰንሰለት ብለን እንጠራዋለን፡፡

ለተወሰነ ጊዜ የሰዎችን ድጋፍ ማግኘት ችግር ባይኖረውም፣ ሃሳባችን የተያዘው ግን በራሳችን መቆም እንደማንችል በመፍራት ከሆነ ይህንን ሰንሰለት የመበጠስን እርምጃ ዛሬውኑ መጀመርና ቀስ በቀስ በራሳችን ወደመቆም እንድናድግ እንመከራለን፡፡

2.  የስሜት ሰንሰለት

ከሰዎች ጋር በስሜት ንክኪ ከተሳሰራችሁና ከእነሱ ውጪ በፍጹም ማሰብም ሆነ መኖር ካቃታችሁ ይህንን ሰንሰለት የስሜት ሰንሰለት ብለን እንጠራዋለን፡፡ ከተቃራኒ ጾታ ጋር በፍቅር መተሳሰርም ሆነ ከአቻዎቻችን ጋር በጓደኝነት መቀራረብ ትክክለኛ ልምምድ ቢሆንም፣ እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር ያላቸውን ትስስር ያቆሙ ጊዜ መኖር እስከሚያስጠላን ድረስ ቀውስ ውስጥ የምንገባ ከሆነ፣ ይህንን ሰንሰለት የመበጠስን እርምጃ ዛሬውኑ መጀመርና ቀስ በቀስ የትኩረት ለውጥ እንድናመጣ እንመከራለን፡፡

ከፈጣሪ ጋር ከቆማችሁ ሙሉ ሰው ናችሁ!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
1.6K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 08:49:00 የደስተኛነታችሁ ጉዳይ

በሕይወታችሁ ለስኬታችሁ ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የደስተኛነታችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ደስተኛነት የየእለት “ሙዳችሁን” ይወስነዋል፡፡ የየእለት “ሙዳችሁ” ደግሞ ሁለት ነገሮችን ይወስናል፡-

1.  ለአንድ ተግባር ያላችሁን መነሳሳት

2.  ከሰዎች ጋር የሚኖራችሁን ግንኙነት

በሕይወታችሁ የምትሰሯቸው ነገሮች “በሙዳችሁ” ምክንያት ካልተሳኩ፡፡ እንዲሁም ያላችሁ ማሕበራዊ ግንኙነት በዚሁ “የሙድ” መዛባት ምክንያት ከተበላሸ - ምን ቀራችሁ?

የደስታችሁ ሁኔታ በየእቱ ሊለዋወጥ የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ልኩን ጠብቆ እንዲቆይ ከፈለጋችሁ . . .

1.  ከሰዎች የምትጠብቁትን (Expect የምታደርጉትን) ነገር ሚዛናዊ አደርጉ፡፡

ሰዎች ሁል ጊዜ ሰዎች ናቸው፡፡ እኛ የምንጠባበቀውን ቀርቶ ቃል የገቡትን ነገር እንኳን ላይፈጽሙት ይችላሉ፡፡ ልባችንን ሙሉ ለሙሉ ከሰዎቹ በምንጠባበቀው ነገር ላይ ከጣልን የስሜት ቀውስ የማይቀር ነው፡፡ ያለፈው ታሪካችሁን መለስ ብላች ካስታወሳችሁ፣ የብዙ የስሜት ቀውስና የተስፋ መቁረጥ መንስኤዎች ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር ያለማግኘታችን ጉዳይ እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡

2.  መለወጥ ወይም መቆጣጠር ከማትችሉት ነገር ላይ ትኩረታችሁን አንሱ፡፡

አንድ ነገር እንደሚሆን ካሰባችሁ ወይም ከሆነባችሁ የመጀመሪያው ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ያንን ነገር መቆጣጠር ወይም መለወጥ የመቻላችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም ብታደርጉ የማትለውጡት ነገር ከሆነ፣ አንደኛችሁን ትኩረታችሁን ከዚያ ነገር ላይ በማንሳት ወደ አስፈላጊው ነገር ላይ እንድታደርጉ ትመከራላቸሁ፡፡ መለወጥ የማትችሉትን ነገር ሲያብሰለስሉ መዋል መለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ እዳትሰሩ ጉልበታችሁን ይወስደዋል፡፡ 

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
3.2K viewsedited  05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 12:30:56 ከባዶ ላይ መዝገን
ደራሲ -ያዕቆብ ብርሀኑ
ተራኪ-አንዱለም ተስፋዬ

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
4.8K viewsedited  09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 12:12:28 የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን!

ይህንን አባባል ካነበብኩት ብዙ ዓመት ሆኖኛል። አባባሉ እንዴት እንዳነቃኝ አልነግራችሁም። በየትኛውም አገልግሎት የራስን ዓቅም መገንባትና በብልጫ ለየት ብሎ መገኘት ጥቅሙ የትየለሌ ነው።

የኮካ ኮላ ጠርሙስ አንዱ በሌላው ያለችግር ይተካል፣ ተመሳሳይ ነው። የኮካ ኮላ ጠርሙስ ይመስል ከሌላው ልዩነት የሌለው ሆኖ መታየት ዓቅመ-ቢስ ያደርጋል።

አንተ ግን የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን! አገልግሎትህ፣ ሥራህ፣ ችሎታህ ከሌላው የተለየ እንዲሆን ሁሌም ራስህን አሻሽል።

የትኛውም ገበያ ለየት ላለ ሥራና አገልግሎት በብልጫ ይከፍላል። ካልከፈለህ የገበያ ቦታህን ቀይርና ትክክለኛ ዋጋህን ከሚያውቁና ከሚከፍሉህ ጋር ሥራ፣ ተገበያይ።

ደሞዝ ጭማሪ ለመጠየቅ ከፈራህ ዓቅምህ በቅጡ አልተገነባም ማለት ነውና አርፈህ ዓቅምህን ገንባ። ዓቅምህን ሳትገነባ ጭማሪ ክፈሉኝ ማለት ልክም ተገቢም አይደለም።

ዓቅምህ የተገነባ ሆኖ በበቂ ካልከፈሉህ ግን የሥራ ቦታህን ወይም የግብይት ቦታና የአሻሻጥ መንገድህን ቀይር። ሁሉም ነገር ስልት አለው።

ልብ በል! በገበያው ላይ ገንዘብ ሞልቷል። በበቂ የማይከፍሉህ "አይገባህም" ብለው ስለሚያስቡ ነው። እንደሚገባህ ማሳየት ደግሞ ያንተ ፋንታ ነው።

Focus on the Value you bring to the market.

#Value_Proposition_Matters!

Via ኢንጂነር ጌቱ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
886 views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 20:33:15 ትምህርት ሰፍቷል ስብዕናችን ወርዷል
ቡርሀን አዲስ
ክፍል -1
አቅራቢ -ትዕግስት አንተንጉስ

ክፍል-2

@zephilosophy
@zephilosophy
2.3K viewsedited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ