Get Mystery Box with random crypto!

የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን! ይህንን አባባል ካነበብኩት ብዙ ዓመት ሆኖኛል። አባባሉ እንዴት እንዳ | የስብዕና ልህቀት

የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን!

ይህንን አባባል ካነበብኩት ብዙ ዓመት ሆኖኛል። አባባሉ እንዴት እንዳነቃኝ አልነግራችሁም። በየትኛውም አገልግሎት የራስን ዓቅም መገንባትና በብልጫ ለየት ብሎ መገኘት ጥቅሙ የትየለሌ ነው።

የኮካ ኮላ ጠርሙስ አንዱ በሌላው ያለችግር ይተካል፣ ተመሳሳይ ነው። የኮካ ኮላ ጠርሙስ ይመስል ከሌላው ልዩነት የሌለው ሆኖ መታየት ዓቅመ-ቢስ ያደርጋል።

አንተ ግን የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን! አገልግሎትህ፣ ሥራህ፣ ችሎታህ ከሌላው የተለየ እንዲሆን ሁሌም ራስህን አሻሽል።

የትኛውም ገበያ ለየት ላለ ሥራና አገልግሎት በብልጫ ይከፍላል። ካልከፈለህ የገበያ ቦታህን ቀይርና ትክክለኛ ዋጋህን ከሚያውቁና ከሚከፍሉህ ጋር ሥራ፣ ተገበያይ።

ደሞዝ ጭማሪ ለመጠየቅ ከፈራህ ዓቅምህ በቅጡ አልተገነባም ማለት ነውና አርፈህ ዓቅምህን ገንባ። ዓቅምህን ሳትገነባ ጭማሪ ክፈሉኝ ማለት ልክም ተገቢም አይደለም።

ዓቅምህ የተገነባ ሆኖ በበቂ ካልከፈሉህ ግን የሥራ ቦታህን ወይም የግብይት ቦታና የአሻሻጥ መንገድህን ቀይር። ሁሉም ነገር ስልት አለው።

ልብ በል! በገበያው ላይ ገንዘብ ሞልቷል። በበቂ የማይከፍሉህ "አይገባህም" ብለው ስለሚያስቡ ነው። እንደሚገባህ ማሳየት ደግሞ ያንተ ፋንታ ነው።

Focus on the Value you bring to the market.

#Value_Proposition_Matters!

Via ኢንጂነር ጌቱ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence