ቢታነፅ ቢወቀር! (በእውቀቱ ስዩም) እኔም አንድ ሰሞን ልክ እንደ ሰለሞን "ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል" እያልሁ አጨልሜ በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር! ከዚያ አንቺን አገኘሁ በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ መፈጠሬን ወደድሁ ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ "ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ! ለካስ... ጠቢብ ቢያስተምረው መከራ ቢመክረው አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር! #share Join: @Human_Intelligence 12.6K views16:30