Get Mystery Box with random crypto!

ኔትወርካቸው እንደነበረ ነው። የጥቅም ትስስሩን ባለሀብቶቻቸው አስቀጥለውታል። በፈለጉት ላይ የፈለገ | ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

ኔትወርካቸው እንደነበረ ነው። የጥቅም ትስስሩን ባለሀብቶቻቸው አስቀጥለውታል። በፈለጉት ላይ የፈለገትን ለማድረግ የከረመ ልምድ አላቸው። ከሀሰት ምስክር እስከ ማስፈረድ የሚደርስ አቅም። ፍትህን ሀብታሞቻቸው በገንዘብ ተከፋዮቻቸው ደግሞ በጩኸት ይቀብሯታል። ፅንፈኛው ይመታህና ይከስሃል። ከዚያ ያሳስርሀል። በአንዲስአበባ በብዙ ቦታዎች እየሆነ ያለው ይህ ነው። የሚታሰረው ሌላ ነው። የተበደለው ሌላ ነው።

በጠሮ ኡስማን ኢብኑ አፋን መስጅድም የሆነው ይህ ነው። በጠሮ መስጂድ በሚገኙ በ5 አባቶችና ኡስታዞች ላይ የ3 አመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል!

ፍትህ ፍትህ ፍትህ

ፅንፈኛው እየሄደበት ያለው የረቀቀ አካሄድ የተቀናጀና በበጀት የታገዘ ለይቶ የማጥቃት ነጥሎ የማሰሰር እያሳሰረ በጩኸትና በገንዘብ ፍትህን መደበቅ ተክኖበታል። ያሳዝናል። በጣም ያሳዝናል።

Adugnaw Muche

تعليق
Note:-ፅንፈኛው =አህባሽ