Get Mystery Box with random crypto!

ጠሮ መስጂድ ላይ የተፈጠረው ምንድን ነው =============================== የ | ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

ጠሮ መስጂድ ላይ የተፈጠረው ምንድን ነው
===============================
የአሕባሽ ባለሃብቶች የበፊት ሰንሰለታቸውን ተጠቅመው ከአሐዳዊ የሙስሊም ጠል አመራር ጋር በማሴር የ3 አመት ጽኑ እስራት በንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የማስፈረድ አቅም እንደት አገኙ?

ህፃን ሴት የደፈረ ባለጌ በ6 አመት እስራት ወዘተ በሚጨመላለቅበት ተጨባጭ፤ ምን ወንጀል ሠርተው ነው 3 አመት የተፈረደባቸው?

እነርሱ እንደሚሉት ዲናችንን እንማራለን በማለታቸው ውሃብያ ስላሏቸው ብቻ አሕባሽ አለመሆን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ እንደት 3 አመት ይፈረድባቸዋል?

መጅሊሱስ ይሄን ጉዳይ ለምን በዝምታ አለፈው ዝም ካላለ ምን እየሠራ ነው? ምክንያቱም ብዙ ስሞታዎች በዚህ ጉዳይ ከአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ በአካል ቀርበውለታል።

አሁንም አልረፈደም። ያለ አንዳች ወንጀላቸው በግፈኞች የሴራ ሰንሰለት የተፈረደባቸው ንጹሐን ወንድሞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነፃ ተብለው በምትኩ ግፈኛ አሳሳሪዎች፣ የሐሰት መስካሪዎችና ያለ አግባብ ፈራጅ የሆኑ በደለኛ ዳኞች ተጠያቂ መደረግ አለባቸው።


አስቸኳይ ፍትሕ ለጠሮ መስጂዶች ወንድሞቻችንና ኡስታዞች

Cc:
===
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Addis Ababa Police

#ሼር_አርጉ
⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊱⊰