Get Mystery Box with random crypto!

የፖሊስ ሀይሎች በታቀደ እና በተጠና መልኩ ሆን ተብሎ ዝግጅት ተደርጎበት በንጽኋን ላይ ፍጅት ፈጽመ | ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

የፖሊስ ሀይሎች በታቀደ እና በተጠና መልኩ ሆን ተብሎ ዝግጅት ተደርጎበት በንጽኋን ላይ ፍጅት ፈጽመዋል

ማስረጃውን እነሆ :-
=================================
በትላትናው ዕለት በአንዋር መስጅድ ንጽኋን ላይ ሆን ተብሎ በታቀደ መልኩ የተፈጸመው የሽብር ተግባር መጀመሪያውኑ ታቅዶበት ፣በቂ ዝግጅት ተደርጎበት የተፈጸመ ተግባር ነው ።
ይህንን ተግባር ለመፈጸም በመጀመሪያ ደረጃ አልሞ ተኳሾች የሚቆሙባቸው ህንጻዎች በእለተ ጁምዓ የታቀደው የሽብር ተግባር እስኪፈጸም ድረስ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው ። ለአብነት ያህል ተወከል ህንጻ አክሲዮን ማህበር እና ድር ተራ አክሲዮን ማህበራት በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ዝግ እንደ ሚሆኑ አስታወቁ ። የህንጻዎቹን አናት በመጠቀም ለታሰበው የሽብር ተግባር ዝግጁ ሆኑ ማለት ነው ።

ይህንን የሽብር ተግባር ዝግጅት የተረዳው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምንም አይነት ተቃውሞ የማይደረግ መሆኑ ተገለጸ ። ነገር ግን የሽብር ተግባሩ ከመጀመሪያው የታቀደበት ነበር እና በንጽኋን ላይ የፍጅት ተግባር ተፈጸመ ። እውነታው ይኼው ነው
መታወቅ ያለበት ነገር ግን በንደዚህ አይነት የሽብር ተግባር ፈጽሞ ሀገር ማረጋጋት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ።
(አብዱረሂም አህመድ)