Get Mystery Box with random crypto!

ሙዓዝ ኢብን ጀበል ለነብዩ (ﷺ) ጀነት አስገብቶ ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ አላቸው። | ጥበብ እና ኢስላም

ሙዓዝ ኢብን ጀበል ለነብዩ (ﷺ) ጀነት አስገብቶ ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ አላቸው።

እሳቸውም እንዲህ አሉ፦”በእርግጥም ትልቅ ነገር ጠይቀሃል። ነገሩ ደግሞ አላህ ላቀለለለት ቀላል ነው።

አላህን ምንም ሳታጋራ ታመልከዋለህ። ሶላትን ቀጥ አድርገህ ትሰግዳለህ። ዘካን ታወጣለህ። ረመዳንን ትጾማለህ። የአላህን ቤት ትጎበኛለህ።”

ከዚያም እንዲህ አሉ “የመልካም በሮችን ላመላክትህ ?

ጾም ጋሻ ነው። ሰደቃና በሌሊት የሚሰገድ ሶላት ደግሞ ልክ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ስህተትን ያጠፋሉ።”

ከዛም ይህንን አነበቡ


تَتَجَافَىٰ جُنُوبُهُمْ عَنِ الْمَضَاجِعِ يَدْعُونَ رَبَّهُمْ خَوْفًا وَطَمَعًا وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፡፡ ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ፡፡


فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም ፡፡

ከዚያም እንድህ አሉ ሰለ ነገሮች ሁሉ ራስ፣ ስለ ምሶሰው እና ስለ ሻኛው ጫፍ ምን እንደሆኑ አልነግርህምን ?” አዎን ንገሩኝ አለ። ነብዩ (ﷺ) እንዲህ አሉ “

የነገራት ሁሉ ራስ እስልምና ነው። ምሶሰውም ሶላት ነው። የሻኛው ጫፍ ደግሞ ጅሃድ ነው።”

ከዚያም እንዲህ አሉ “ይህንን ሁሉ ጠቅልሎ የሚይዘውን አልነግርህምን ?” አዎን ንገሩኝ አለ።

ምላሳቸውን ያዙና “ይህንን ተጠንቀቅ” አሉ። እኔም በምንናገረው ነገር እንጠየቃለን እንዴ አልኳቸው?እሳቸውም “እናትህ ትጣህና (እንዲከሰት ተፈልጎ አይደለም ልብ በሉት)ሰዎች በፊቶቻቸው እሳት ውስጥ የሚወረወሩት በምላሳቸው ውጤት አይደለምን ?”

ሓዲሱን ቲርሚዚይ ዘግቦታል።

https://t.me/httpstebebinaeslam