Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95% የሚሆነውን ማስመለስ ቻለ፡፡
**********
ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7፣ 2016 ዓ.ም በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801,417,747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር የተገለጸ ሲሆን ከዚህም ገንዘብ ላይ ብር 762,941,341 ማስመለስ ችሏል፡፡ ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 5 በመቶ ብር 38,474,938 ገንዘቡን ተመላሽ ካላደረጉ ግለሰቦች የማስመለስ ሥራው እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡