Get Mystery Box with random crypto!

ሚያዝያ 12፤2016 - በአዲስ አበባ ከተማ በተገነቡ ማዕከላት ከመደበኛው ገበያ የጤፍ ዋጋ ላይ የ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ሚያዝያ 12፤2016 - በአዲስ አበባ ከተማ በተገነቡ ማዕከላት ከመደበኛው ገበያ የጤፍ ዋጋ ላይ የ3 ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው ተገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ተገንብተው አምራችን ከሸማቾች የሚያገናኙ ሶስት ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው አሁን ላይ በዋነኛነት የገበያ ማዕከላት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን የተናገሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እንደተገነቡ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በእነዚህ ማዕከላት አምራቾችን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ ለሸማቾች ከማሳ የተሰበሰቡ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ እያቀረበ ነው ብለዋል።እነዚህ ማዕከላት በሸማቹ እና በአምራቹ መሀል የነበረውን ህገ ወጥ ደላላን መስበር የቻለ ነው።

ከዋጋም አኳያ ከእሁድ ገበያ አንፃር የተሻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።ምርቶች በበቂ ሁኔታ በገበያ ማዕከላት ቢገቡም ህብረተሰቡ ስለ ማዕከላቱ በቂ ግንዛቤ ስሌለው የሚበላሹ ምርቶች አሉ በተለይ ደግሞ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ብልሽት እንደሚገጥማቸው ተናግረዋል።

ሸማቹ ወደ እነዚህ ማዕከላት በመምጣት ሁሉንም ምርቶች በአንድ እንዲሁም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።ከመደበኛ ገበያዎች የጤፍ ዋጋ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የ3ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው አንስተዋል። እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችም ከእሁድ ገበያው ቅናሽ እንዳለውም አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

ማዕከላቱ በኮልፌ ፣በአቃቂ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ይገኛሉ ተብሏል።

በምህረት ታደሰ
#BisratFm