Get Mystery Box with random crypto!

በእግረኞች የሚፈጸሙ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች እና የቅጣት መጠን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

በእግረኞች የሚፈጸሙ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች እና የቅጣት መጠን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከመጋቢት 13 ቀን 2016 ጀምሮ እግረኞችን ለመቆጣጠና አደጋ ለመቀነስ ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።

እስካሁን ባለው ሂደት ባለፉት 15 ቀናት ከ700 በላይ እግረኞች በዚህ ደንብ መሰረት መቀጣታቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

አዲስ ማለዳ ከባለስልጣኑ ባገኘችው መረጃ በመንገድ ትራስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት የጥፋት ዓይነት እና የቅጣት መጠን የሚከተሉት ናቸው

ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ ማቋረጥ - 40 ብር
ለተሽከርካሪ በተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት የተጓዘ ወይም የቆመ - 40 ብር
እግረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዝ ይዞ መጓዝ - 40 ብር
ከእግረኛ መንገድ ውጭ መጓዝ - 40 ብር
የእግረኛ መንገድ ላይ ንግድ ማካሄድ፣ ቁሳቁስ ማስቀመጥና ለእግረኞች ጉዞ እንቅፋት መሆን - 80 ብር
በብረትም ሆነ በግንብ የተለየ መንገድ ዘሎ ማቋረጥ - 80 ብር
በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጡ መንገድ ማቋረጥ - 80 ብር
ለእግረኝ ክልክል በሆነ መንገድ፣ በማሳለጫ እና ቀለበት መንገድ ማቋረጥ - 80 ብር

እነዚህ ጥፋቶች ፈጽሞ በገንዘብ መቀጣት የማይችል አልያም የማይፈልግ ማንኛውም እግረኛ ማህበራዊ አገልግሎት ይሰጣል።
- ባለ 40 ብር ቅጣት የ30 ደቂቃ
- ባለ 80 ብር ቅጣት ደግሞ የ1 ሰዓት ማህበራዊ አገልግሎት ይሰጣሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች 80 በመቶ የሚሆነው የሞት አደጋ የሚከሰተው በእግረኞች ላይ ነው።
———
(አዲስ ማለዳ)