Get Mystery Box with random crypto!

የቤት ኪራይ? የቤት ግዢ ? መሬት? ይቀንሳሉ ይጨምራሉ? ሰሞኑን በርካታ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቤት ኪራይ? የቤት ግዢ ? መሬት?
ይቀንሳሉ ይጨምራሉ?

ሰሞኑን በርካታ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች እየወጡ መሆኑን ተከትሎ ከሚዘዋወሩ ጥያቄዎች መካከል የቤት ዋጋ ይቀንሳል ወይስ ይጨምራል? የቤት መግዢያስ ? የመሬት ነገር እንዴት ይሆናል? የሚሉ ግዘፍ ነስተው ወጥተው ይታያሉ።

እኔም በዚህ ጉዳይ የግል ምልከታና ግምቴን ማስቀመጥ ወደድኩ።

በእኔ አመለካከት በአጭሩ የቤት ኪራይ ዋጋ ይጨምራል፣ የቤት መግዣ ዋጋ ይቀንሳል፣ የመሬት ዋጋም እየቀነሰ ይሄዳል የሚል ነው። ለእያንዳድንዳቸው ምክንያቶቼንም እንዲህ አስቀምጣለሁ:-

1) #የቤት_ኪራይ_ዋጋ_ይጨምራል ያልኩባቸው ምክንያቶች
፩) ብዙ ቤቶች ለኪራይ ገበያ እየወጡ ባለመሆኑ
፪) እንደሌሎች ዘርፎች ከመንግስት መመሪያዎች ትይዩ በቤት ባለቤቶች የሚያወጧቸው መሬት ላይ የሚተገበሩ ያልተጻፉ ህጎች ገዢ ስለሚሆኑ
፫) ባለፉት አመታት ዋጋ መጨመርም ሆነ ከቤት ማስወጣት ክልክል በነበረባቸው ወቅቶች የቤት አከራዮችና ተከራዮች ኑሮ ውድነቱን ያማከለ መጨማመርና ልምምድ መኖሩ
፬) ፖሊሲዎችን እንደ ክፍተት የሚጠቀሙ የተከራይ አከራዮች መበራከት (ትልቅ ቤት ተከራይተው ከፋፍለው የሚያከራዩ (House hackers ) መበራከት)
፭) በመኖሪያ ቤትነት ከማከራየት ይልቅ ጥቂት የቤት ዕቃዎችን አሟልተው በእንግዳ ማረፊያ (Guest house) ስም ማከራየት ተመራጭ (ማምለጫም) እየሆና መምጣቱ
፮) ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ወደ መዲናችን በተለያዩ ምክንያቶች ለኑሮ የሚመጡ ወገኖች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ
፯) የጊቢውና ሌሎች ወሳኝ ቦታዎች ቁልፍና የግቢው መተዳደሪያ ህግ በቤቱ ባለቤቶች እጅ መሆኑ :)

2) #የቤት_መግዣ_ዋጋ_ይቀንሳል ለማለት ምክንያቶቼ
፩) የገንዘብ (ካሽ) እጥረት መኖሩ
፪) ብዙ አልሚዎች ዘርፉን መቀላቀላቸው
፫) በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ ቤቶችን በአንድ አካባቢ የሚገነቡ ከተማ አከል የቤት ግንባታዎች ( mass housing projects) መጀማመር
፬) በቴክኖሎጂ የተደገፉ ዋጋ ቀናሽ የቤት አማራጮች እየመጡ መሆኑ
፭) የመሬት አቅርቦት መሻሻል ( በሊዝ፣ በPPP ፣ አብሮ ማልማት...)

3) #የመሬት_ዋጋ_ይቀንሳል ስል ምክንያቶቼ
፩) በርካታ መሬት ወደ ገበያ እየወጣ መሆኑ ( በመንግስት፣ በግለሰቦች፣ በልማት ተነሺዎች፣ በልማት ሰጊዎች :) ...)
፪)የገንዘብ (ካሽ) እጥረት መኖር
፫) ከመግዛት ይልቅ አብሮ ማልማት በቦታ ገዢዎች እየተመረጠ መምጣቱ
፬) የፈረሳ ስጋት መኖር
፭) ከመንግድ ገብቶ መገንባት የሚለው መመሪያ ይየትናንሽ መሬቶችን የመልማት አቅም ስለሚፈታተን
፮) በኮሪደር ልማት ተከትሎ የተቀመጠውን የግንባታና ዲዛይን መስፈርት አሟልቶ መገንባት ለብዙዎች ከባድ መሆኑ
፯) በቂ አቅም ማሳያና ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ለሚያዘጋጁ ቀጥታ ከመንግስት ለማስፋፊያም ሆነ ለአዲስ ፕሮጀክት መሬት የማግኘት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ

በ ደሳለኝ ከበደ።
ሲቪል መሀንዲስ፣ ሪል ስቴት አማካሪ፣