Get Mystery Box with random crypto!

የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ በድርጅቶች የሚከፈለው የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔ 30% (ሰላሳ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ

በድርጅቶች የሚከፈለው የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔ 30% (ሰላሳ በመቶ)ነው::

የቤት ኪራይ ገቢ ግብር እንዴት ይሰላል?
*****
• ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ የሚባለው፤ በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ላይ ነው፡፡

• የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው፤ የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡

• ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት፤ ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር