Get Mystery Box with random crypto!

ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የትራንስፎርመር አቅም ማሻሻያ ስራ እየተከናወነ ነው ለኮዬ ፈጬ ሁለት የጋራ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የትራንስፎርመር አቅም ማሻሻያ ስራ እየተከናወነ ነው

ለኮዬ ፈጬ ሁለት የጋራ መኖሪያ ቤት ሳይቶች ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ትራንስፎርመሮች አቅም ማሻሻያ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡት ግዙፍ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል የኮዬ ፈጬ ሳይት አንዱ ሲሆን ነዋሪዎቹ የመደበኛው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እስኪጠናቀቅ ድረስ በጊዜዊነት የኤሌክትሪክ የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለነዋሪዎቹ እየቀረበ ያለውን አገልግሎት በቂና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችል የትራንስፎርመር አቅም ማሻሻያ ስራ በመከናወን ላይ ሲሆን የማሻሻያ ስራው የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግና አጋዥ ትራንስፎርመር መትከልን የሚያካትት ነው፡፡

እንዲሻሻሉ በጥናት ከተለዩ 30 ትራንስፎርመሮች መካከል በአሁኑ ወቅት የ10 ትራንስፎርመሮች የማሻሻያ ስራ በመከናወን ላይ ሲሆን በቀጣይም የቀሪዎቹ የማሻሻያ ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡

የትራንስፎር ማሻሻያ ስራው 60 ሚሊዮን 583 ሺ 168 ብር ወጪ በመከናወን ላይ ሲሆን የማሻሻያ ስራው ሲጠናቀቅ ነዋሪዎቹ ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት