Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት መርሃ ግብር አካሄደ፤ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት መርሃ ግብር አካሄደ፤
-----------
የከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት በየወቅቱ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን ከዚህ በፊት ለመምህራን ተላልፈው የነበሩ እና በተለያየ መልኩ በህገ ወጥ ተይዘው የነበሩ 435 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመምህራን በእጣ እንዲተላለፉ በመወሰኑ ነው እጣ የማውጣት መርሃ ግብሩ የተካሄደው።

በእጣ አወጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት ከንቲባ አደነች አቤቤ ሀብቶችን በፍትሃዊነት እና በግልጸኝነት ለሁሉም ተጠቃሚነት ማዋል ስለሚገባ ከዚህ በፊት ለመምህራን ተላልፈው ከነበሩ 5ሺ ቤቶች የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ሲነሱባቸው የነበሩ ቤቶች ተጣርተው በግልጸኝነት በእጣ ለመምህራን እንዲተላለፉ መወሰኑን ተናግረዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት የመምህራን ብቻ ሳይሆን የበርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥያቄ ነው ያሉ ሲሆን የመኖሪያ ቤት ጥያቄን መንግስት በሚያቀርበው መርሃ-ግብር ብቻ መመለስ አይቻልም ብለዋል።

በመሆኑም የተለያዩ የቤት አቅርቦት አማራጮች መቀመጣቸውን አና ከነዚህ ውስጥ አንዱ በሆነው በማህበር ተደራጅቶ ቤት የመገንባት አማራጭ መምህራን ቅድሚያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መወሰኑን ከንቲባ አዳነች አስታውቀዋል።

ቤቶቹ በፍትሃዊነት የመምህራኑን የአገልግሎት ዘመን፣ የአካል ጉዳተኞች እንዲሁም የሴቶችን ልዩ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በእጣው የተካተቱ ከ9 ዓመት ጀምሮ እስከ ከ35 ዓመት በላይ በአራት የተለያዩ እርከኖች  አገልግሎት ያላቸው መምህራን በእጣው ውስጥ መካተታቸውም ተገልጿል።