Get Mystery Box with random crypto!

የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና በእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና በእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች እንዲቋረጡ መወሰኑን አሳውቋል።

በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ስር ያሉ ተከሳሾች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ወንጀል ክስ ክርክር ሲካሄድ ነበር።

በሌላ በኩል የእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የክስ መዝገብ በ1ኛ የህገመንግስትና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት የክርክር ሂደት ላይ ቆይቷል።

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር እነዚህ የክስ ሂደቶች "ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም " ሲባል እንዲቋረጡ ተወስኗል ብሏል።