Get Mystery Box with random crypto!

የቤቶች ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ተጠናቀቀ። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቤቶች ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ተጠናቀቀ።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነቧቸውና ለጨረታ ያቀረቧቸው 3,146 የመኖሪያና 306 የንግድ ባጠቃላይ 3,452 ቤቶች የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በዛሬው ዕለት መጋቢት 02/2016 ዓም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት መጠናቀቁ ተገልጿል።

ከጥር 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የሰነድ ሽያጭ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ በነገው ዕለት መጋቢት 03/2016 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ይከፈታል ተብሏል።

በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ለጨረታ የቀረቡት 935 የመኖሪያና 15 የንግድ ቤቶች ላይ ተጫራቾች ያስገቧቸው ሰነዶች በታዛቢዎች ፊት የሚከፈት ይሆናል ተብሏል።