Get Mystery Box with random crypto!

የሚሻለው የህዝብ ጥቆማዎችን መቀበል እና ማጣራት ማድረግ ወይስ ለማዳፈን መሞከር? በቅርቡ በቦሌ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሚሻለው የህዝብ ጥቆማዎችን መቀበል እና ማጣራት ማድረግ ወይስ ለማዳፈን መሞከር?

በቅርቡ በቦሌ ኤርፖርት ባሉ ብልሹ አሰራሮች ዙርያ አንዳንድ መረጃዎችን አጋርቼ ነበር፣ የተወሰኑ እርምጃዎችም እንደተወሰዱ መስማቴን እንዲሁ። በርካታ ሌሎች ግለሶችም 'እኛም ላይ እንዲህ ደርሷል' በማለት ማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃ አጋርተዋል። እኔ ያጋራሁት መረጃ ጉዳይ አየር ማረፊያውን ከሚያስተዳድሩ አካላት ጋር እንጂ ከአየር መንገዱ ጋር በቀጥታ እንደማይገናኝ ለማስረዳት ሞክሬያለሁ።

ይህንን በአራት ባለስልጣናት ዛሬ የተሰጠ መግለጫን ሳነብ መጨረሻ አካባቢ "በኤርፖርት ዙሪያ የወንጀል ተግባራት ላይ በሚሳተፉ ሰዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ተገቢው  ማጣራት ተደርጎ  ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል" ይላል። መልካም።

ይሁንና ቅሬታው በቀጥታ በአየር መንገዱም ዙርያ ቢሆንም ጥቆማዎችን አመስግኖ ተቀብሎ ማጣራት ማድረግ ይገባል እንጂ ለማዳፈን መሞከር አይጠቅምም።

ይበልጥ የሚገርመው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወሮ ሰላማዊት ዳዊት ለኢቢሲ "የስራ ጫና በሚኖርበት ወቅት ችግር የሚፈጥሩ ሰራተኞች እንዳሉ እንገነዘባለን" ብለው ትናንት ተናግረው ነበር።

ነገር ግን ሀላፊዋ በልጁ ላይ በቅርቡ የተፈፀመ እንግልትን መረጃ ያጋራ አቶ ነብዩ ሲራክ የተባለ ግለሰብ ጋር ስልክ በመደወል "ሚዲያ ላይ መወራቱ ማንንም አይጠቅምም፣ ምናልባት እናንተን ታዋቂ popular ሊያደርጋችሁ ይችል ይሆናል፣ ተቋሙ ያለ መረጃ መሰደብ የሌለበት ተቋም ነው" እንዳሉት መረጃ አጋርቷል።

ከህዝብ የሚደርሱ ቅሬታዎች እና ጥቆማዎች ለለውጥ ለሚሰራ አካል መሻሻሎችን ለማድረግ ከፍተኛ ግብዐቶች ናቸው፣ የስም መነሳት ብቻ ለሚያሳስበው አካል ግን ትንኮሳዎች እና የስም ማጥፋት ድርጊቶች ናቸው።

1/2