Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ፍቅር ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ ሰላም ለመላው የዓለም ህዝብ ይሁን:: ለስኳር በሽ | መርጌታ አለምአየሁ

ሰላም
ፍቅር
ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ ሰላም ለመላው የዓለም ህዝብ ይሁን::

ለስኳር በሽታ የሚከለከሉ አመጋገብ

#የህክምና ባለሙያዎችም ቅድመ ስኳርን ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤን እና አመጋገብን ማስተካከል እንደሚገባ ይመክራሉ።
ከዚህ አንጻር አንድ ሰው የቅድመ ስኳር ምልክት በታየበት ጊዜ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ምግቦች ባይመገብ ይመረጣል፤

የፍራፍሬ ጭማቂ

#የፍራፍሬ ጭማቂ የበዛ ስኳርና የያዘና በጥሬው ከሚመገቡት ፍራፍሬ በበለጠ ጣፋጭ በመሆኑ በቅድመ ስኳር ምልክት ወቅት መመገቡ ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድልን ስሚያሰፋ አይመከርም።

አልኮል መጠጥ

የአልኮል መጠጦች በውስጣቸው ያለው የስኳር መጠን ቢለያይም የስኳር በሽታ ታጋላጭነትን ያሰፋሉ።
አልኮል የሚጠጡ ሰዎች አንድም በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል አልያም በተቃራኒው ይወርዳል።
ይህ ደግሞ የቅድመ ስኳር ምልክት ለታየባቸው ሰዎች እጅጉን አደገኛ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ለዚህም አልኮልን ማስወገድ አልያም የስኳር መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ እንደ ወይን ያሉ የአልኮል መጠጦችን በውሃ በመበረዝ መጠቀም።

ቅባት የዛባቸው ምግቦች

ቅባት የበዛባቸው ምግቦች የኢንሱሊንን ስራ በማስተጓጎል የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ሊጨምሩ ይችላሉ።

ጣፋጭ (ስኳር የበዛባቸው) ምግቦች

#ስኳር ለሰውነታችን አስፈላጊ ቢሆንም በብዛት መውሰድ ግን ለስኳር ህመም ተጋላጭ ስለሚያደርገን በቅድመ ስኳር ህመም ወቅት ማስወገድ ይገባናል።
ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ካስፈለገም ከተዘጋጁ በኋላ ሳይሆን በጥሬው (በፍራፍሬ) መልክ ቢመገቡ ከጣፋጭ ምግቦች ማግኘት የሚገባዎትን በቂ የስኳር መጠን ያገኛሉ።
ባለሙያዎቹ ጣፋጭ ምግቦችን አለመመገብ ሳይሆን መመጠኑን ይመክራሉ።

ሩዝ፣ ነጭ ዱቄትና ዳቦ

#ሌላው እና በቅድመ የስኳር ወቅት መዘውተር የሌለበት ምግብ ደግሞ ሩዝ እና ከስንዴ የሚዘጋጅ ነጭ ስንዴና ዳቦዎችን ነው።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ነጭ ዱቄት በፋብሪካ በሚመረትበት ወቅት በሚኖረው የማቀነባበር ሂደት ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ያጣል።
በዚህ ሂደት የሚቀረው ነገር የስኳር መጠኑ ብቻ በመሆኑም የቅድመ ስኳር ምልክት በሚታይ ጊዜ መጠቀሙ አደጋ እንዳለው ይገልጻሉ።

የስኳር ብሽታን እንዴት እናስታግስ?

የአያቶቻችን እውቀት እንዲህ ይላል::

የሴት ዕሬት ግንድ ጭማቂ
ከአብሽ ጭማቂ ጋር

መጠናቸው
#የዕሬቱ ጭማቂ ግማሽ የውኃ ብርጭቆ
#የአብሽ ጭማቂ ግማሽ የውኃ ብርጭቆ

አንድ ላይ በማቀላቀል ጧት ጧት በባዶ ሆድ አንድ አንድ ብርጭቆ ለሰባት ቀን ይውሰዱ::

ውጤቱን ከሳምንት በኃላ በማየት ምስክር ይሁኑ::
በአማን ዘተፈትነ!!!

የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ ስልኮች በስራ ሰዓት ይደውሉልኝ::

09 12 99 97 05