Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሰላም ጤና እድገት ብልፅግና በያላች | መርጌታ አለምአየሁ

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት በሀገራችን ኢትዮጵያና በዓለም ሁሉ ላላችሁ ሕዝቦች በሙሉ ተመኘሁላችሁ ።

ዛሬ ስለአንድ ተአምረኛ የዓይነ ጥላ ማስወገጃ እፅዋት አጠቃቀም ትንሽ ላጋራችሁ።

#አስተናግር (ማየ ዘለፋ) በወሎ ባድማ ጠባቂ ይባላል ።

አስተናግር በሊቃውንቶች ሲቀመም ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው እፅዋት ነው።

#ለትምህርት ( ለአፍልሆ )
#ለአይነ ጥላ ማስወገጃ
#ለዛር መንፈስ ማስወገጃ
#አይምሮውን ለነሳው(ላበደሰው )
#ለልጅ ጥላ በሽታ
#ለአልማዝ ባለጭራ በሽታ
#ለልጆች የራስ አጓጎት(ቁስል )
#ለአስም በሽታ
#ለአፍንጫ አላርጅክ
#ለመወፍረ እስኪት
#ለስንፈተ ወሲብ
#ለችፌ በሽታ
#ለከበሮ እደ ጥበብ ወዘተ ለመሳሰሉት ያገለግላል ።

፩#ዓይነ ጥላ ለማስለቀቅ ስሩን ሰብስቦ ቀጥቅጦ አድርቆ ከፍሬው ጋር በመጨመር ከ 7 -14 ቀን አንዳንድ የስኳር ማንኪያ እየታጠኑ መተኛት።

፪#ለአልማዝ ባለጭራ ቅጠሉን አሽቶ ጨምቆ የታመመውን አካል መቀባት ።

፫#ለልጆች የራስ አጓጎት ቅጠሉን አሽቶ ጨምቆ አጓጎቱን መቀባት።

፬#ለችፌ ፍሬውን በብዛት ሰብስቦ ፈጭቶ የታመመውን አካል በቅቤ እየለወሱ እስኪድን መቀባት።

፭#ለስንፈተ ወሲብ ከእፀ ሳቤቅ ቅጠል ጋር አሽቶ ጨምቆ በውሀው ብልትን ለሰባቶ ቀን እየቀቡ መተኛት ።

፮#ለአስም በሽታ ቅጠሉን አድርቆ እንደሲጃራ በወረቀት አዘጋጅቶ በእሳት እየለኮሱ ጭሱን መሳብ ።

፯#ለአፍንጫ አላርጅክ ቅጠሉን አሽቶ ውሀውን ተንጋሎ በአፍንጫ መሳብ ።

፰#ላበደ ሰው ፍሬውን አልሞ ሁለት ያሻህይ ማንኪያ ዱቄት በ2 ሾርባ ማንያ ማር በጥብጦ ማጠጣት ጥበቃ ያስፈልገዋል አይምሮውን ይመልስለታል።

ሌሎች ገቢሮች በጥበበኛ ሰው ቢሰሩ ይመረጣል ።

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።
ጥበብ ታላቋን ታከብራለች

ለችግረኛ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ #ሸር #share ማድረግዎን እንዳይረሱ

➤ የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይቀርባል ይብራራል

ጥበብ ታላቋን ታከብራች

በቤትዎ ሁነው ጥበብን ይማሩ እውቀትን ይሸምቱ

የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይቀርባል ይብራራል


09 12 99 97 05
በስራ ሰዓት ይደውሉ