Get Mystery Box with random crypto!

#ሰላም #ፍቅር #ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እንዲሁም ለውድ የሰው ልጅ ይሁን። ጭርት / Tinea | መርጌታ አለምአየሁ

#ሰላም
#ፍቅር
#ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እንዲሁም ለውድ የሰው ልጅ ይሁን።

ጭርት / Tinea corporis/

ጭርት በፈንገስ ምክንያት በቆዳ ላይ የሚከሰት የኢንፌክሽን ዓይነት ነዉ፡፡ የጭርት መገለጫዉ ክብ የሆነ ዳር ዳሩ ቀይና መሃሉ የዳነ የሚመስል ሲሆን የማሳከክ ስሜት ሊኖረዉም ላይኖረዉም ይችላል፡፡ ጭርት ካንዱ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቆዳ ለቆዳ ንክኪ በቀላሉ የሚተላለፍ የህመም አይነት ነዉ፡፡

ምልክቶች

ጭርት ቅርፊታማና ጠፍጣፋ ሆኖ በቆዳ ላይ የሚወጣና አንዳንዴ የማሳከክ ባህሪና ቀላ ያለ ቁስለት ያለዉ፤ ክብ ሆኖ ጠርዝ ጠርዙ ቀይ መልክ የሚኖረዉ እና ቀስ በቀስ እየሰፋ የሚመጣ የቆዳ ላይ ህመም ነዉ፡

የመተላለፊያ መንገዶች

• ከሰዉ ወደ ሰዉ፡- ጭርት በአብዛኛዉን ጊዜ የሚተላለፈዉ ኢንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር ቀጥታ የቆዳ ንክኪ በሚኖርበት ወቅት ነዉ፡፡

• ከእንስሳት ወደ ሰዉ፡- ጭርት የያዘዉ እንስሳ ካለና ንክኪ ከነበረዎ ጭርት ሊተላለፍብዎ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከዉሻ፣ ድመት

• ከእቃ ወደ ሰዉ፡- የቆደ ላይ ጭርት ያለበት ሰዉ/እንስሳ በጭርት እጁ ወይም ቢታከክበትና ሌላ ሰዉ ያንን እቃ ቢነካዉ ጭርት ሊተላለፍበ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ልብስ፣ ፎጣ፣ የአልጋ ልብስ/አንሶላ፣ የፀጉር ማበጠሪያና ብሩሾች ይጠቀሳሉ፡፡

• ከአፈር ወደ ሰዉ፡- እንዳንዴ ጭርት ከተበከለ አፈር ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነዉ ከተበከለ አፈር ጋር ለረጅም ጊዜ ንክኪ ካለዎ ነዉ፡፡

ለጭርት ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች

• እድሜያቸዉ ከ15 ዓመታት በታች የሆኑ ህፃናት
• እርጥበታማ፣ እምቅ አየርና በተፋፈገ ሁኔታ ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ
• በጭርት በተያዘ ሰዉ/እንስሳ ጋር የቅርብ ግንኙነት/ንክኪ ያለዎ ከሆነ
• የፈንገስ እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር አልባሳት፣ አንሶላ ወይም ፎጣ በጋራ መጠቀም
• በጣም ጥብቅ ያሉና አየር በቀላሉ የማይዘዋወርባቸዉ አልባሳትን የሚያዘወትሩ ከሆነ ለጭርት በሽታ ተጋላጭነትዎ ሰፊ ይሆናል።

ይህ ምልክት በትንሹ የጭርት ምልክት በህክምና ባለሙያዎች የተቀመጠ ምልክት ሲሆን!
ከስር የጭር መፍትሔ በሊቃውንት የተከተበ ፍቱን መፍትሔ እንሆ!

#የጭርት መፍትሔ

#የበለስ ቅጠል
#የክትክታ ቅጠል

እነዚህ ዕጽዋቶች ቅጠላቸው በብዛት በማሰባሰብ ለየብቻ አድርቀው ተፈጭተው በደንብ አድርገው በመንፋት አንድ ላይ በመቀላቀል!
አንድ ትንሽ ማንኪያ ከተቀላቀውለ መድኃኒት በንፁህ የፀጉር ቅቤ በመለወስ ጧት ጧት ፀሐይ ለሰዓታት መሞቅ ሙሉ መፍትሔ ይሰጣል።

ለበለጠ መረጃ 0912999705 በስራ ሰዓት ይደውሉ።

#የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

09 12 99 97 05