Get Mystery Box with random crypto!

ትክ ብዬ ሳየው የጥርሷን ድርዳሮ ያደላትን ከንፈር እንዴት ችሎ ይሆን ይህን እፁብ ገላ የሚውጠው | ግጥም ፍቅር ቅኔ

ትክ ብዬ ሳየው
የጥርሷን ድርዳሮ ያደላትን ከንፈር
እንዴት ችሎ ይሆን
ይህን እፁብ ገላ የሚውጠው አፈር
እልና አንድ ቀን
በሌላ እለት ደግሞ
የጠጉሯ ጉንጉን ፏፏቴ ይመስለኛል
ልቤ ሞኝ ነገር
ጠጉሯን ተንተርሶ መተኛት ይመኛል
ቀናቶች ሲከንፉ መወደስ ላይበቃት
እያየው ስትገርመኝ
እያየው ሳደንቃት
.
አንድ ቀን ሰልችቶኝ
እንደ አደይ ከፈካ
ከደመቀ ህይወቷ -- ውበቷን ሳወጣው
ከህይወቷ መዝገብ
የምደነቅበት ቅንጣት ነገር አጣው

የጥርሷ ድርዳሮ
አሰልፎ ይገላል
የራሷ አቀማመጥ
ብርቱካን ይመስላል
ውበቷን ሳወድስ.. ሳደናንቅ ብልም
የሚያምረው 'ራሷ
ጠጉር ማብቀል እንጂ
ማሰብን አይችልም
ከዛን ቀን ጀምሮ
ቆንጆ ሴት ስትቀርበኝ
ከውበቷ በላይ የሚታየኝ አልፎ
ውጪው የተኳለ ውስጡ ባዶ ቀፎ!
.
.
*------------------*
(በሚኪያስ ፈይሣ)