Get Mystery Box with random crypto!

ከናቷ ማጀት ይንፎለፎላል የዱአው ማዳ እሷም ወርቅ ነች አሚን ነዉ ቃሏ ለአመት ሚበጃት ስንቋን | ግጥም ፍቅር ቅኔ

ከናቷ ማጀት
ይንፎለፎላል የዱአው ማዳ
እሷም ወርቅ ነች
አሚን ነዉ ቃሏ
ለአመት ሚበጃት ስንቋን ትትቀዳ!

''ሙሲባ ይራቅ
ቤታችን ይሳቅ
ለጠላን ሁሉ ሙሀባ አይንሳዉ
ጨለማን ገፎ በሁብ ያስደሳዉ
ያዉ እኛዉ ላይ ነዉ
በእዉር ሲመራ ሚተራመሰዉ...''

አሚን ትላለች
እሷም ያሚን ልጅ
ከዱካክ ሁሉ የምት'ፈርጅ
ከደጅ ለመጣ
ተጇ ባይኖራት ምሰጥ ብታጣ
ከወረሰችዉ
ከጀባዉ ቀድታ የምታጠጣ

''ማድሽ አይጉደል
ሸርሽ አይብቀል
ባፉታ ታጥቦ
ይስጠም ከ ገደል''

አሚን ትላለች!
ሃጃ ጉዳይዋ
ታሚን አይፈቅም እሱን ታዉቃለች!

''እንባሽ አይርከስ
ላዘንሽ ቀርቶ ለደስታሽ ይፍሰስ
ዳኢም ስትስቂ
በረሱል ናፍቆት ተነሽ እለቂ''

አሚን ነዉ ዉሏ
ሌላም አደለ ምርኩዝ አመሏ...
አጂብ ነዉ ከቶ!!
ተናቷ ፈልቃ
ፍቅር መስጠትን ለብሳ እንደ ሽቶ...
ሊገላት መቶ
ለኒካህ ሾማት
በዱአ ሰክሮ ላ'አሚኗ ሞቶ!


አሚን በሉማ(ልዩ ሞላ)

ኒካህ=ቀለበት
ሙሲባ=ክፉ