Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ ማለት ለኔ ፅጌረዳ አበባ ፣ የውበት ማህደር፤ የፍቅር መስህብ ፣ የጨዋነት መንደር፤ የድን | ግጥም ፍቅር ቅኔ

አንቺ ማለት ለኔ

ፅጌረዳ አበባ ፣ የውበት ማህደር፤
የፍቅር መስህብ ፣ የጨዋነት መንደር፤
የድንቅ ፈጣሪ...ዕፁብ ድንቅ ፍጡር፤
የሄዋን ብርቅ ዘር ፣ የደስደስ ዋንጫ፤
የቁምነገር ጎጆ ፣ የውበት ማጌጫ፤
የፈገግታየ ምንጭ ፣ የሳቄ ባለቤት፤
ያይኖቸላይ ስዕል ፣ የልቤላይ ንግስት፤
የኔነቴ ግማሽ ፣ የሂወቴ F i K i R፤
የመኖሬ ትርጉም ፣ የደስታየ ሚስጥር፤
አምላክ ለኔ ብሎ ፣ ከአጥንቴ የሰራሽ፤
ሞቸም የማፈቅርሽ ፣ የግራ ጎኔ ነሽ።

KeyD