Get Mystery Box with random crypto!

(ሀገሬ) ግጥሜን ሳነብልሽ፣ በብራና ዓለም ሙያሽ ተዘክሮ ፣ አያልቅም ለዘላለም | ግጥም ፍቅር ቅኔ

(ሀገሬ)
ግጥሜን ሳነብልሽ፣ በብራና ዓለም
ሙያሽ ተዘክሮ ፣ አያልቅም ለዘላለም

ለምን ካልሽኝ?
የሚስጥር ካዝና ነሽ፣መቼም ማትሰለቺ
እንባዬን አብሰሽ፣ ችግር የምትፈቺ

የብዙሃን ጎጆ፣ ስምሽ የረቀቀ
በጥላቻ መንፈስ፣ ክንድሽ ያልወደቀ

እፅዋቶችሽም እድሜ ጠገብ ናቸው
ስራቸው ያማረ ፣ ቀን የወጣላቸው

አዎ ውዷ ሀገሬ - - -
ትውልዱን አንፀሽ ፣ ታሪክ ጦምረሻል
እንክርዳዱን ትተሽ፣ ስንዴውን ዘርተሻል

በአረንጓዴ አሻራ ፣ ተስፋሽን ሰንቀሽ
እይኸው እስከዛሬ ፣ ታሸበርቂያለሽ።

እናም ውዷ ሀገሬ - - -
ቃላትም የለኝም ፣ ስለ አንቺ የሚያወራ
ሀዘንሽ ይቀረፍ ፣ ይውጣልሽ እንጀራ ።
# ቤዚቾ